Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 42:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የም​ን​ሄ​ድ​በ​ትን መን​ገ​ድና የም​ና​ደ​ር​ገ​ውን ነገር ይን​ገ​ረን።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 አምላክህ እግዚአብሔር ወዴት መሄድ እንዳለብንና ምን ማድረግ እንደሚገባን እንዲነግረን ጸልይልን።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ጌታ አምላክህም የምንሄድበትን መንገድና ማድረግ የሚገባንን ነገር ያሳውቀን ይሆናል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ስለዚህ አምላክህ እግዚአብሔር በየት አቅጣጫ መሄድ እንዳለብንና ምን ማድረግ እንደሚገባን ይገልጥልን ዘንድ ጸልይልን።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 42:3
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በመንገድህ ሁሉ ጥበብን ዕወቃት፥ እርስዋም መንገድህን ታቃናልሃለች።


ከጽዮን ሕግ፥ ከኢየሩሳሌምም የእግዚአብሔር ቃል ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ ሄደው፦ ኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፥ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ በፍለጋውም እንሄዳለን ይላሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በመ​ን​ገድ ላይ ቁሙ ተመ​ል​ከ​ቱም፤ የቀ​ደ​መ​ች​ው​ንም መን​ገድ ጠይቁ፤ መል​ካ​ሚቱ መን​ገድ ወዴት እንደ ሆነች ዕወቁ፤ በእ​ር​ስ​ዋም ላይ ሂዱ፤ ለነ​ፍ​ሳ​ች​ሁም መድ​ኀ​ኒ​ትን ታገ​ኛ​ላ​ችሁ፤” እነ​ርሱ ግን፥ “አን​ሄ​ድ​ባ​ትም” አሉ።


በአ​ም​ላ​ካ​ችን ፊት ራሳ​ች​ንን እና​ዋ​ርድ ዘንድ፥ ከእ​ር​ሱም የቀ​ና​ውን መን​ገድ ለእ​ኛና ለል​ጆ​ቻ​ችን፥ ለን​ብ​ረ​ታ​ች​ንም ሁሉ እን​ለ​ምን ዘንድ በዚያ በአ​ኅዋ ወንዝ አጠ​ገብ ጾምን አወ​ጅሁ።


ሕግ ከጽ​ዮን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይወ​ጣ​ልና ብዙ​ዎች አሕ​ዛብ መጥ​ተው፥ “ኑ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ፥ ወደ ያዕ​ቆብ አም​ላክ ቤት እን​ውጣ፤ እር​ሱም መን​ገ​ዱን ያስ​ተ​ም​ረ​ናል፤ በጎ​ዳ​ና​ውም እን​ሄ​ዳ​ለን” ይላሉ።


አንተ በሰ​ማይ ስማ፤ የሚ​ሄ​ዱ​በ​ት​ንም መል​ካም መን​ገድ በማ​ሳ​የት የባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህ​ንና የሕ​ዝ​ብ​ህን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ኀጢ​አት ይቅር በል፤ ለሕ​ዝ​ብ​ህም ርስት አድ​ር​ገህ ለሰ​ጠ​ሃት ምድር ዝና​ብን ስጥ።


ለእ​ነ​ርሱ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ለል​ጆ​ቻ​ቸው መል​ካም ይሆ​ን​ላ​ቸው ዘንድ፥ እን​ዲ​ፈ​ሩኝ፥ ሁል​ጊ​ዜም ትእ​ዛ​ዜን ሁሉ እን​ዲ​ጠ​ብቁ እን​ዲህ ያለ ልብ ማን በሰ​ጣ​ቸው፥


ከሥጋ ለባሽ ሁሉ እኛ እንደ ሰማን በእ​ሳት መካ​ከል ሆኖ ሲና​ገር የሕ​ያው አም​ላ​ክን ድምፅ ሰምቶ በሕ​ይ​ወት የኖረ ማን ነው?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች