Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 41:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እስ​ማ​ኤል የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በሀ​ገሩ ላይ የሾ​መ​ውን የአ​ኪ​ቃ​ምን ልጅ ጎዶ​ል​ያ​ስን ስለ ገደ​ለው ከለ​ዳ​ው​ያ​ንን ፈር​ተ​ዋ​ልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ወደ ግብጽም የሄዱት ከባቢሎናውያን ለማምለጥ ነበር፤ ባቢሎናውያንንም የፈሩት የናታንያ ልጅ እስማኤል የባቢሎን ንጉሥ የምድሪቱ ገዥ አድርጎ የሾመውን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በመግደሉ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ምክንያቱም የናታንያ ልጅ እስማኤል የባቢሎን ንጉሥ በአገሩ ላይ የሾመውን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን ስለ ገደለው ከለዳውያንን በመፍራታቸው ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እስማኤል የባቢሎን ንጉሥ በአገሩ ላይ የሾመውን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን ስለ ገደለው ከለዳውያንን ፈርተዋልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 41:18
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እር​ሱም ገና ሳይ​መ​ለስ፥ “የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በይ​ሁዳ ከተ​ሞች ላይ ወደ ሾመው ወደ ሳፋን ልጅ ወደ አኪ​ቃም ልጅ ወደ ጎዶ​ል​ያስ ተመ​ለስ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር በሕ​ዝቡ መካ​ከል በይ​ሁዳ ምድር ተቀ​መጥ፤ ወይም ትሄድ ዘንድ ለዐ​ይ​ንህ ደስ ወደ​ሚ​ያ​ሰ​ኝህ ስፍራ ሂድ” አለው። የአ​ዛ​ዦ​ችም አለቃ ስን​ቅና ስጦታ ሰጥቶ አሰ​ና​በ​ተው።


እና​ንተ የም​ት​ፈ​ሩት ሰይፍ በዚያ በግ​ብፅ ምድር ያገ​ኛ​ች​ኋል፤ ስለ እር​ሱም የም​ት​ደ​ነ​ግ​ጡ​በት ራብ በዚያ በግ​ብፅ ይደ​ር​ስ​ባ​ች​ኋል፤ በዚ​ያም ትሞ​ታ​ላ​ችሁ።


ከም​ት​ፈ​ሩት ከባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ፊት አት​ፍሩ፤ አድ​ና​ችሁ ዘንድ፥ ከእ​ጁም አስ​ጥ​ላ​ችሁ ዘንድ እኔ ከእ​ና​ንተ ጋር ነኝና አት​ፍሩ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሐሰት የተ​ና​ገ​ር​ሽው፥ እኔ​ንም ያላ​ሰ​ብ​ሽው፥ በል​ብ​ሽም ነገ​ሩን ያላ​ኖ​ር​ሽው ማንን ሰግ​ተሽ ነው? ማን​ንስ ፈር​ተሽ ነው? እኔም ዝም አል​ሁሽ፤ አን​ቺም አል​ፈ​ራ​ሽ​ኝም።


በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ግን የመ​ን​ግ​ሥት ዘር የነ​በረ የኤ​ል​ሴማ ልጅ የና​ታ​ንዩ ልጅ እስ​ማ​ኤል መጣ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ዐሥር ሰዎች ነበሩ፤ ጎዶ​ል​ያ​ንም መታው፤ ሞተም፤ ከእ​ር​ሱም ጋር በመ​ሴፋ የነ​በ​ሩ​ትን አይ​ሁ​ድ​ንና ከለ​ዳ​ው​ያ​ን​ንም ገደ​ላ​ቸው።


የጭ​ፍራ አለ​ቆ​ችም ሁሉ፥ የቃ​ር​ሔም ልጅ ዮሐ​ናን፥ የሐ​ና​ንያ ልጅ ኢዛ​ን​ያስ ሕዝ​ቡም ሁሉ ከታ​ናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ወደ ነቢዩ ወደ ኤር​ም​ያስ መጡ።


የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በይ​ሁዳ ምድር በቀ​ረው ሕዝብ ላይ የሳ​ፋ​ንን ልጅ የአ​ኪ​ቃ​ምን ልጅ ጎዶ​ል​ያን ሾመው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች