Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 41:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 የቃ​ር​ሔም ልጅ ዮሐ​ናን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት የጭ​ፍራ አለ​ቆች ሁሉ የአ​ኪ​ቃ​ምን ልጅ ጎዶ​ል​ያ​ስን በመ​ሴፋ ከገ​ደ​ለው በኋላ ከና​ታ​ንያ ልጅ ከእ​ስ​ማ​ኤል ያስ​መ​ለ​ሱ​አ​ቸ​ውን የሕ​ዝ​ቡን ቅሬታ ሁሉ፥ ከገ​ባ​ዖን ያስ​መ​ለ​ሱ​አ​ቸ​ውን ኀያ​ላን ሰል​ፈ​ኞ​ችን፥ ሴቶ​ች​ንም፥ ልጆ​ች​ንም፥ ጃን​ደ​ረ​ቦ​ች​ንም ወሰዱ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 የቃሬያ ልጅ ዮሐናንና ከርሱ ጋራ የነበሩት የጦር መኰንኖች ሁሉ የናታንያ ልጅ እስማኤል የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን ከገደለ በኋላ፣ በምጽጳ ከማረካቸው የተረፉትን ሰዎች በማስመለስ ይዘው ሄዱ፤ እነዚህም፣ ወታደሮች፣ ሴቶች ሕፃናትና ከገባዖን ያመጧቸው የቤተ መንግሥት ባለሥልጣኖች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 የቃሬያም ልጅ ዮሐናን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን ከገደለ በኋላ እርሱና ከእርሱም ጋር የነበሩት የጭፍራ አለቆች ሁሉ ከናታንያ ልጅ ከእስማኤል ከምጽጳ ያስመለሱአቸውን የሕዝቡን ትሩፍ ሁሉ፥ እንዲሁም ከገባዖን ያስመለሱአቸውን ወታደሮች፥ ሴቶችንም፥ ልጆችንም፥ ጃንደረቦችንም፥ ወሰዱ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከዚህ በኋላ ዮሐናንና ከእርሱ ጋር ያሉት የሠራዊቱ መሪዎች፥ እስማኤል ገዳልያን ከገደለ በኋላ ከምጽጳ ማርኮ የወሰዳቸውን ወታደሮች፥ ሴቶች፥ ሕፃናትና ጃንደረቦች ሁሉ መለሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 የቃሬያም ልጅ ዮሐናን ከእርሱም ጋር የነበሩት የጭፍራ አለቆች ሁሉ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በምጽጳ ከገደለው በኋላ ከናታንያ ልጅ ከእስማኤል ያስመለሱአቸውን የሕዝቡን ቅሬታ ሁሉ፥ ከገባዖን ያስመለሱአቸውን ሰልፈኞች፥ ሴቶችንም፥ ልጆችንም፥ ጃንደረቦችንም፥ ወሰዱ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 41:16
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የቃ​ር​ሔ​ም​ንም ልጅ ዮሐ​ና​ንን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩ​ትን የጭ​ፍራ አለ​ቆች ሁሉ፥ ከታ​ናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ ጠራ፤


እስ​ማ​ኤ​ልም በመ​ሴፋ የነ​በ​ረ​ውን የሕ​ዝ​ቡን ቅሬታ ሁሉ፥ የን​ጉ​ሡን ሴቶች ልጆች፥ የአ​ዛ​ዦች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ለአ​ኪ​ቃም ልጅ ለጎ​ዶ​ል​ያስ የሰ​ጠ​ውን በመ​ሴፋ የቀ​ሩ​ትን ሕዝብ ሁሉ መለሰ፤ የና​ታ​ን​ያም ልጅ እስ​ማ​ኤል ወደ አሞን ልጆች ይሄድ ዘንድ ተነሣ።


የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለ​ቆች ሁሉ ሰዎ​ቻ​ቸ​ውም፥ የና​ታ​ንዩ ልጅ እስ​ማ​ኤል፥ የቃ​ሬ​ያን ልጅ ዮሐ​ናን፥ የነ​ጦ​ፋ​ዊ​ውም የተ​ን​ሑ​ሜት ልጅ ሴሪያ፥ የማ​ዕ​ካ​ታ​ዊው ልጅ አዛ​ንያ፥ ሰዎ​ቻ​ቸ​ውም የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ጎዶ​ል​ያን እንደ ሾመው በሰሙ ጊዜ ወደ ጎዶ​ልያ ወደ መሴፋ መጡ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች