Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 4:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ምድ​ሪ​ቱን ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ እነ​ሆም ባዶ ነበ​ረች፤ ሰማ​ያ​ት​ንም ተመ​ለ​ከ​ትሁ፤ ብር​ሃ​ንም አል​ነ​በ​ረ​በ​ትም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ምድርን ተመለከትሁ፤ እነሆ ቅርጽ የለሽና ባዶ ነበረች፤ ሰማያትንም አየሁ፣ ብርሃናቸው ጠፍቷል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ምድሪቱን አየሁ፥ እነሆም፥ ባዶ ነበረች አንዳችም አልነበረባትም፤ ሰማያትንም አየሁ፥ ብርሃንም አልነበረባቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ምድርን ተመለከትኩ፤ እነሆ ባድማ ሆናለች፤ ሰማይንም ተመለከትኩ፤ እነሆ ብርሃን አይታይበትም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ምድሪቱን አየሁ፥ እነሆም፥ ባዶ ነበረች አንዳችም አልነበረባትም፥ ሰማያትንም አየሁ፥ ብርሃንም አልነበረባቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 4:23
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ከዚያች ወራትም መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ይጨልማል፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤


የሰ​ማ​ይም ከዋ​ክ​ብ​ትና ኦሪ​ዎን፥ የሰ​ማይ ሠራ​ዊ​ትም ሁሉ ብር​ሃ​ና​ቸ​ውን አይ​ሰ​ጡም፤ ፀሐ​ይም በወ​ጣች ጊዜ ትጨ​ል​ማ​ለች፤ ጨረ​ቃም በብ​ር​ሃኑ አያ​በ​ራም።


ምድር ግን ባዶ ነበ​ረች፤ አት​ታ​ይ​ምም ነበር፤ የተ​ዘ​ጋ​ጀ​ችም አል​ነ​በ​ረ​ችም፤ ጨለ​ማም በው​ኃው ላይ ነበረ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በው​ኃው ላይ ይሰ​ፍፍ ነበር።


በዚ​ያም ቀን ፀሐይ በቀ​ትር ይገ​ባል፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ብር​ሃ​ንም በም​ድር ላይ በቀን ይጨ​ል​ማል።


ምድ​ሪ​ቱም ከፊ​ታ​ቸው ትደ​ነ​ግ​ጣ​ለች፤ ሰማ​ይም ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣል፤ ፀሐ​ይና ጨረ​ቃም ይጨ​ል​ማሉ፤ ከዋ​ክ​ብ​ትም ብር​ሃ​ና​ቸ​ውን ይሰ​ው​ራሉ።


በዚ​ያም ቀን እንደ ባሕር መት​መም ይተ​ም​ሙ​ባ​ቸ​ዋል፤ ወደ ምድ​ርም ይመ​ለ​ከ​ታሉ፤ ድቅ​ድቅ ጨለ​ማን ያያሉ፤ ይጨ​ነ​ቃ​ሉም።


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።


ታላቅና ነጭ ዙፋንን በእርሱም ላይ የተቀመጠውን አየሁ፤ ምድርና ሰማይም ከፊቱ ሸሹ፤ ስፍራም አልተገኘላቸውም።


በተ​ራ​ሮቹ ላይ አል​ቅሱ፤ በም​ድረ በዳም ጎዳና ላይ እዘኑ፤ ሰው ጠፍ​ት​ዋ​ልና፤ የሚ​መ​ላ​ለ​ስም የለ​ምና ሙሾ​ው​ንም አሙሹ፤ የሰ​ማይ ወፍ ድም​ፅ​ንም እስከ ከብት ድምፅ ድረስ አይ​ሰ​ሙም፤ ደን​ግ​ጠ​ውም ተማ​ር​ከው ሄዱ።


ሰማይ በዚህ ደነ​ገጠ፤ እጅ​ግም ተን​ቀ​ጠ​ቀጠ” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ብር​ሃን ወደ​ሌ​ለ​በት ወደ ጨለማ መርቶ ወሰ​ደኝ።


በዚያም ቀን በረዶና ውርጭ እንጂ ብርሃን አይሆንም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች