Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 39:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 የይ​ሁዳ ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያ​ስና ሰል​ፈ​ኞ​ቹም ሁሉ በአ​ዩ​አ​ቸው ጊዜ፥ በሌ​ሊት ሸሹ፤ በን​ጉ​ሡም አት​ክ​ልት መን​ገድ በሁ​ለቱ ቅጥር መካ​ከል በነ​በ​ረው ደጅ ከከ​ተ​ማ​ዪቱ ወጡ፤ በዓ​ረ​ባም መን​ገድ ወጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስና ወታደሮቹ ሁሉ እነርሱን ባዩ ጊዜ ሸሹ፤ በሌሊት በንጉሡ አትክልት ስፍራ በኩል አድርገው በሁለቱ ቅጥር መካከል ከከተማዪቱ ወጡ፤ ወደ ዓረባም አመሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ወታደሮቹም ሁሉ ባዩአቸው ጊዜ ኰበለሉ፥ በሌሊትም በንጉሡ አትክልት መንገድ በሁለቱ ቅጥሮች መካከል በነበረው በር በኩል ከከተማይቱ ወጡ፤ መንገዳቸውንም ወደ ዓረባ አድርገው ተጓዙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ንጉሥ ሴዴቅያስና ወታደሮቹ ሁሉ የሆነውን ነገር ባዩ ጊዜ በሌሊት ከከተማይቱ ወጥተው ለማምለጥ ሞከሩ፤ በቤተ መንግሥቱ የአትክልት ቦታ በኩል አድርገው ሁለቱን ቅጽሮች በሚያገናኘው መውጫ በር አቋርጠው ወደ ዮርዳኖስ ሸለቆ አቅጣጫ አመለጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ሰልፈኞቹም ሁሉ ባዩአቸው ጊዜ ኰበለሉ፥ በሌሊትም በንጉሡ አትክልት መንገድ በሁለቱ ቅጥር መካከል ከነበረው ደጅ ከከተማይቱ ወጡ፥ በዓረባም መንገድ ወጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 39:4
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሚ​ሮጥ ሰው ማም​ለጥ አይ​ች​ልም፤ ኀይ​ለ​ኛ​ውም በብ​ር​ታቱ አይ​ዝም፤ አር​በ​ኛ​ውም ነፍ​ሱን አያ​ድ​ንም።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ሰው​ነ​ቱን አጽ​ናና፤ የፈ​ረ​ሰ​ው​ንም ቅጥር ሁሉ ጠገነ፤ በላ​ዩም ግንብ ሠራ​በት፤ ከእ​ር​ሱም በስ​ተ​ውጭ ሌላ ቅጥር ሠራ፤ ወደ ዳዊ​ትም ከተማ የሚ​ያ​ወ​ጣ​ውን በር አጠ​ነ​ከረ፤ ብዙም መሣ​ሪ​ያና ጋሻ አዘ​ጋጀ።


በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም የሚ​ኖ​ረው አለቃ በት​ከ​ሻው ላይ አን​ግቶ በጨ​ለማ ይወ​ጣል፤ በዚያ ያወጡ ዘንድ ግን​ቡን ይነ​ድ​ላሉ፤ በዐ​ይ​ኑም ምድ​ርን እን​ዳ​ያይ ፊቱን ይሸ​ፍ​ናል።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጠ​ላ​ቶ​ችህ ፊት የተ​መ​ታህ ያደ​ር​ግ​ሃል፤ በአ​ንድ መን​ገድ ትወ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ በሰ​ባት መን​ገ​ድም ከእ​ነ​ርሱ ትሸ​ሻ​ለህ፤ በም​ድ​ርም መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ የተ​በ​ተ​ንህ ትሆ​ና​ለህ።


በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ምድ​ሮች ሳሉ ከእ​ና​ንተ ተለ​ይ​ተው በቀ​ሩት ላይ በል​ባ​ቸው ድን​ጋ​ጤን እሰ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በነ​ፋ​ስም የም​ት​ን​ቀ​ሳ​ቀስ የቅ​ጠል ድምፅ ታሸ​ብ​ራ​ቸ​ዋ​ለች፤ ከሰ​ይፍ እን​ደ​ሚ​ሸሹ ይሸ​ሻሉ ፤


ፊቴ​ንም አከ​ብ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ፊት ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ፤ የሚ​ጠ​ሏ​ች​ሁም ያሸ​ን​ፉ​አ​ች​ኋል። ማንም ሳያ​ሳ​ድ​ዳ​ችሁ ትሸ​ሻ​ላ​ችሁ።


በአ​ሮ​ጌው ኵሬ ላለው ውኃ በሁ​ለቱ ቅጥር መካ​ከል መከ​ማቻ ሠራ​ችሁ፤ ይህን ያደ​ረ​ገ​ውን ግን አል​ተ​መ​ለ​ከ​ታ​ች​ሁም፤ ቀድሞ የሠ​ራ​ው​ንም አላ​ያ​ች​ሁም።


የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያስ በእ​ው​ነት በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ አልፎ ይሰ​ጣል፤ አፍ ለአ​ፍም ይና​ገ​ረ​ዋል፤ ዐይን ለዐ​ይ​ንም ይተ​ያ​ያሉ እንጂ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን እጅ አያ​መ​ል​ጥም፤


ቀን ለቀ​ንም በፊ​ታ​ቸው እክ​ት​ህን እንደ ስደ​ተኛ እክት አው​ጣው፤ በማ​ታም ጊዜ በዐ​ይ​ና​ቸው እያ​ዩህ ስደ​ተ​ኞች እን​ደ​ሚ​ወጡ እን​ዲሁ ውጣ።


ነገር ግን አለ​ቆ​ችሽ ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ሸሹ፤ የተ​ማ​ረ​ኩ​ት​ንም በእ​ግር ብረት አሠ​ቃ​ዩ​አ​ቸው፤ ኀይ​ለ​ኞ​ች​ሽም ርቀው ሸሹ።


አር​ኤ​ል​ንም አስ​ጨ​ን​ቃ​ለሁ፤ ይህ​ችም ኀይል፥ ይህ​ችም ብዕል የእኔ ትሆ​ና​ለች፥


ሴዴ​ቅ​ያ​ስም ወደ ባቢ​ሎን ይገ​ባል፤ እኔም እስ​ክ​ጐ​በ​ኘው ድረስ በዚያ ይኖ​ራል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ጋር ብቷጉ ምንም አይ​ቀ​ና​ች​ሁም።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች