Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 39:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ አለ​ቆች ሁሉ፥ ማር​ጋ​ና​ሳር፥ ሳማ​ጎት፥ ናቡ​ሳ​ኮር፥ ናቡ​ሰ​ሪስ፥ ናግ​ራ​ጎ​ስ​ና​ሴር፥ ረብ​ማግ፥ ኔር​ጋል ሴሪ​አ​ጼር፥ ከቀ​ሩት ከባ​ቢ​ሎን ንጉሥ አለ​ቆች ሁሉ ጋር ገብ​ተው በመ​ካ​ከ​ለ​ኛው በር ውስጥ ተቀ​መጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የባቢሎን ንጉሥ መኳንንት ሁሉ፦ የሳምጋሩ ኤርጌል ሳራስር፣ ጠቅላይ አዛዡ ናቦሠርሰኪም፣ ከፍተኛው ሹም ኤርጌል ሳራሳር እንዲሁም ሌሎቹ የባቢሎን ንጉሥ መኳንንት ሁሉ ገብተው በመካከለኛው በር ተቀመጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ኢየሩሳሌምም በተያዘች ጊዜ የባቢሎንም ንጉሥ አለቆች ሁሉ፥ ኤርጌል ሳራስር፥ ሳምጋር ናቦ፥ የራፌሱ ሠርሰኪም፥ የራብማጉ ኤርጌል ሳራስር፥ ከተረፉት ከባቢሎን ንጉሥ አለቆች ሁሉ ጋር ገብተው በመካከለኛው በር ውስጥ ተቀመጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 የኢየሩሳሌም ከተማ በተያዘች ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ ባለ ሥልጣኖች መጥተው በመካከለኛው ቅጽር በር ስፍራ ስፍራቸውን ያዙ፤ ከእነርሱም መካከል፥ ኔርጋልሻሬጼር፥ ሣምጋር ነቦ፥ ሣርሰኪምና ሌላው ኔርጋልሻሬጼርና እንዲሁ ሌሎችም ይገኙባቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 የባቢሎንም ንጉሥ አለቆች ሁሉ፥ ኤርጌል ሳራስር፥ ሳምጋርናቦ፥ ሠርሰኪም፥ ራፌስ፥ ኤርጌል ሳራስር፥ ራብማግ፥ ከቀሩት ከባቢሎን ንጉሥ አለቆች ሁሉ ጋር ገብተው በመካከለኛው በር ውስጥ ተቀመጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 39:3
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኤር​ም​ያ​ስም ሴዴ​ቅ​ያ​ስን፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ አለ​ቆች ብት​ወጣ፥ ነፍ​ስህ በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ለች፤ ይህ​ችም ከተማ በእ​ሳት አት​ቃ​ጠ​ልም፤ አን​ተም፥ ቤት​ህም በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ላ​ችሁ።


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ በቅ​ጥ​ርም ውጭ የከ​በ​ቡ​አ​ች​ሁን ከለ​ዳ​ው​ያ​ንን የም​ት​ወ​ጉ​በ​ትን በእ​ጃ​ችሁ ያለ​ውን የጦር መሣ​ሪ​ያ​ች​ሁን እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እነ​ዚ​ያ​ንም በዚ​ህች ከተማ መካ​ከል እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።


የአ​ዛ​ዞች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳ​ንም ላከ፤ ናቡ​ሻ​ዝ​ባ​ንም፥ ራፋ​ስ​ቂ​ስም፥ ኔር​ጋል ሴራ​አ​ጼ​ርም፥ ራብ​ማ​ግም፥ የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ አለ​ቆች ሁሉ ላኩ።


እነሆ እኔ በሰ​ሜን ያሉ​ትን የመ​ን​ግ​ሥ​ታ​ቱን ወገ​ኖች ሁሉ እጠ​ራ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እነ​ር​ሱም ይመ​ጣሉ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ውም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በር መግ​ቢያ በዙ​ሪ​ያ​ዋና በቅ​ጥ​ርዋ ሁሉ ላይ፥ በይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች ሁሉ ላይ ዙፋ​ና​ቸ​ውን ያስ​ቀ​ም​ጣሉ።


የባ​ቢ​ሎ​ንም ሰዎች ሴኬ​ቤ​ቴ​ና​ሆ​ምን ሠሩ፤ የኩ​ታም ሰዎች ኤር​ጌ​ትን ሠሩ፤


ከፈ​ረ​ሶ​ቹም ብዛት የተ​ነሣ በት​ቢያ ይሸ​ፍ​ን​ሻል፤ ከሠ​ረ​ገላ መን​ኰ​ራ​ኵ​ርና ከፈ​ረ​ሶቹ ድምፅ የተ​ነ​ሣም ቅጥ​ሮ​ች​ሽን ያፈ​ር​ሳል፤ ወን​በዴ መሣ​ሪ​ያ​ውን ይዞ ወደ ምድረ በዳ ቦታ እን​ዲ​ገባ በሮ​ች​ሽን ይገ​ቡ​ባ​ቸ​ዋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች