Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 32:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 እና​ን​ተም፦ ያለ ሰውና ያለ እን​ስሳ ያለች ባድማ ናት፤ ለከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም እጅ ተሰ​ጥ​ታ​ለች በም​ት​ሉ​አት ምድር እር​ሻን እንደ ገና ይገ​ዛሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 እናንተም፣ “ለባቢሎናውያን ዐልፋ ስለ ተሰጠች፣ ሰውና እንስሳ የማይኖሩባት ባድማ ናት” ባላችኋት በዚህች ምድር እንደ ገና መሬት ይገዛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 እናንተም፦ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ያለች ባድማ ናት፥ ለከለዳውያንም እጅ ተሰጥታለች በምትሉአት ምድር እርሻን ይገዛሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 ‘ምድሪቱ ለባቢሎናውያን ስለ ተሰጠች ሰዎችም ሆኑ እንስሶች የማይኖሩባት ባድማ ትሆናለች’ ባላችኋት በዚህች ምድር የእርሻ መሬት መግዛትና መሸጥ እንደገና ይጀመራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 እናንተም፦ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ያለች ባድማ ናት፥ ለከለዳውያንም እጅ ተሰጥታለች በምትሉአት ምድር እርሻን ይገዛሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 32:43
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ሰዎች በዚህ ምድር ቤት​ንና እር​ሻን የወ​ይን ቦታ​ንም እንደ ገና ይገ​ዛሉ።”


አን​ተም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! እር​ሻ​ውን በብር ግዛ፤ ምስ​ክ​ሮ​ች​ንም ጥራ አል​ኸኝ፤ እኔም ውሉን ጽፌ አተ​ምሁ፤ ምስ​ክ​ሮ​ች​ንም አቆ​ምሁ፤ ከተ​ማ​ዪቱ ግን ለከ​ለ​ዳ​ው​ያን እጅ ተሰ​ጥ​ታ​ለች።”


አሁን እን​ግ​ዲህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንተ ስለ እር​ስዋ፥ “በሰ​ይ​ፍና በራብ በቸ​ነ​ፈ​ርም ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ ትሰ​ጣ​ለች ስለ​ም​ት​ላት ከተማ እን​ዲህ ይላል፦


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እና​ንተ፦ ያለ ሰውና ያለ እን​ስሳ ያለች ባድማ ናት በም​ት​ሉ​አት በዚች ስፍራ፥ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ቸው በሌለ፥ ያለ ሰውና ያለ እን​ስሳ ባድማ በሆኑ በይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ፥


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ባድማ ሆኖ፥ ያለ ሰውና ያለ እን​ስሳ ባለው በዚህ ስፍራ በከ​ተ​ሞ​ችም ሁሉ መን​ጎ​ቻ​ቸ​ውን የሚ​ያ​ሳ​ር​ፉ​በት የእ​ረ​ኞች መኖ​ሪያ ይሆ​ናል።


ተዘ​ል​ለ​ውም ይቀ​መ​ጡ​ባ​ታል፤ ቤቶ​ች​ንም ይሠ​ራሉ፤ ወይ​ኑ​ንም ይተ​ክ​ላሉ፤ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም በአሉ በሚ​ን​ቋ​ቸው ሁሉ ላይ ፍር​ድን በአ​ደ​ረ​ግሁ ጊዜ ተዘ​ል​ለው ይቀ​መ​ጣሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ቸው፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አም​ላክ እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች