Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 32:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 አን​ተም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! እር​ሻ​ውን በብር ግዛ፤ ምስ​ክ​ሮ​ች​ንም ጥራ አል​ኸኝ፤ እኔም ውሉን ጽፌ አተ​ምሁ፤ ምስ​ክ​ሮ​ች​ንም አቆ​ምሁ፤ ከተ​ማ​ዪቱ ግን ለከ​ለ​ዳ​ው​ያን እጅ ተሰ​ጥ​ታ​ለች።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 አንተ ግን ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከተማዪቱ ለባቢሎናውያን ዐልፋ እየተሰጠች፣ ‘መሬቱን በብር ግዛ፤ ግዥውንም በምስክሮች ፊት ፈጽም’ ትለኛለህ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ምንም እንኳ ከተማይቱ ለከለዳውያን እጅ ተላልፋ ብትሰጥም፤ አቤቱ ጌታ ሆይ! አንተ ግን፦ “እርሻውን በብር ግዛ ምስክሮችንም ጥራ” አልኸኝ።’ ”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ከተማይቱ በባቢሎናውያን ልትያዝ ተቃርባ ሳለ መሬቱን በምስክሮች ፊት እንድገዛ ያዘዝከኝ አንተ ነህ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 አንተም፥ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፦ እርሻውን በብር ግዛ ምስክሮችንም ጥራ አልኸኝ፥ ከተማይቱ ግን ለከለዳውያን እጅ ተሰጥታለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 32:25
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዲህ ብለው አሙት፦ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድረ በዳ ማዕ​ድን ያሰ​ናዳ ዘንድ


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማዳ​ኑን አሳየ። በአ​ሕ​ዛ​ብም ፊት ቃል ኪዳ​ኑን ገለጠ።


ለእ​ነ​ርሱ፥ ለዘ​ራ​ቸ​ውና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ከሰ​ጠ​ኋ​ቸው ምድር እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ሰይ​ፍ​ንና ራብን ቸነ​ፈ​ር​ንም እሰ​ድ​ዳ​ለሁ።”


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ሰዎች በዚህ ምድር ቤት​ንና እር​ሻን የወ​ይን ቦታ​ንም እንደ ገና ይገ​ዛሉ።”


አሕ​ዛ​ብም መጥ​ተው ይህ​ችን ሀገር ያዟት፤ ይህ​ችም ከተማ ከረ​ኃ​ቡና ከጦሩ የተ​ነሣ በወ​ጓት በከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሰዎች እጅ ወደ​ቀች፤ እንደ ተና​ገ​ር​ኸ​ውም ሆነ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


እና​ን​ተም፦ ያለ ሰውና ያለ እን​ስሳ ያለች ባድማ ናት፤ ለከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም እጅ ተሰ​ጥ​ታ​ለች በም​ት​ሉ​አት ምድር እር​ሻን እንደ ገና ይገ​ዛሉ።


እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል የአ​ጎቴ ልጅ አና​ም​ኤል እኔ ወደ አለ​ሁ​በት ወደ ግዞቱ ቤት አደ​ባ​ባይ መጥቶ፥ “በብ​ን​ያም ሀገር በዓ​ና​ቶት ያለ​ውን እር​ሻ​ዬን ግዛ፤ የመ​ግ​ዛ​ትና የመ​ው​ረስ መብቱ የአ​ንተ ነውና፥ አንተ ታላ​ቃ​ችን ነህና፤ ለአ​ንተ ግዛው” አለኝ። ይህም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ ሆነ ዐወ​ቅሁ።


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰው ሁሉ ለወ​ን​ድ​ሙና ለባ​ል​ን​ጀ​ራው ዓመተ ኅድ​ገ​ትን ለማ​ድ​ረግ እኔን አል​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ እነሆ እኔ ለሰ​ይ​ፍና ለቸ​ነ​ፈር፥ ለራ​ብም ዓመተ ኅድ​ገ​ትን አው​ጅ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በም​ድ​ርም መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ መካ​ከል እበ​ት​ና​ች​ኋ​ለሁ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔ የም​ሠ​ራ​ውን አንተ ዛሬ አታ​ው​ቅም፤ ኋላ ግን ታስ​ተ​ው​ለ​ዋ​ለህ” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች