Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 22:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ወደ ይሁዳ ንጉሥ ቤት ውረድ፤ በዚ​ያም ይህን ቃል ተና​ገር፥ እን​ዲ​ህም በል፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ወደ ይሁዳ ንጉሥ ቤተ መንግሥት ውረድ፤ ይህንም መልእክት በዚያ እንዲህ ብለህ ተናገር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ጌታ እንዲህ አለ፦ “ወደ ይሁዳ ንጉሥ ቤት ውረድ በዚያም ይህን ቃል ተናገር፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1-2 እግዚአብሔር የዳዊት ዘር ወደ ሆነው ወደ ይሁዳ ቤተ መንግሥት እንድወርድና በዚያም ለንጉሡ፥ ለመኳንንቱና ለኢየሩሳሌም ሕዝብ እኔ የምነግራቸውን ቃል እንዲያዳምጡ እንዲህ ብለህ ንገራቸው አለኝ፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ቤት ውረድ በዚያም ይህን ቃል ተናገር፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 22:1
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሂድ፤ ለይ​ሁ​ዳም ንጉሥ ለሴ​ዴ​ቅ​ያስ ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በለው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ይች ከተማ በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ ተላ​ልፋ ትሰ​ጣ​ለች፤ ይይ​ዛ​ታል፤ በእ​ሳ​ትም ያቃ​ጥ​ላ​ታል።


ዮሐንስ ሄሮድስን “የወንድምህ ሚስት ለአንተ ልትሆን አልተፈቀደም፤” ይለው ነበርና።


ነገር ግን ቤቴል የን​ጉሥ መቅ​ደ​ስና የመ​ን​ግ​ሥት ቤት ናትና ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በዚህ ደግሞ ትን​ቢት አት​ና​ገር” አለው።


ካህ​ናት ሆይ! ይህን ስሙ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! አድ​ምጡ፤ የን​ጉሥ ቤት ሆይ! ልብ አድ​ርጉ፤ ለሚ​መ​ለ​ከት ወጥ​መድ፥ በታ​ቦ​ርም ላይ የተ​ዘ​ረጋ አሽ​ክላ ሆና​ች​ኋ​ልና ፍርድ በእ​ና​ንተ ላይ ነው።


የይ​ሁዳ ንጉሥ ቤት ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምና​ሴ​ንና ሕዝ​ቡን ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ግን አል​ሰ​ሙ​ትም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ነቢዩ ናታ​ንን ወደ ዳዊት ላከ፤ ወደ እር​ሱም መጥቶ አለው፥ “በአ​ንድ ከተማ አንዱ ባለ​ጠጋ፥ አን​ዱም ድሃ የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩ።


እንደ ሥራ​ች​ሁም ፍሬ እቀ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዱ​ር​ዋም ውስጥ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ በዙ​ሪ​ያ​ዋም ያለ​ውን ሁሉ ይበ​ላል።”


በዳ​ዊት ዙፋን የም​ት​ቀ​መጥ የይ​ሁዳ ንጉሥ ሆይ! አን​ተና አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በእ​ነ​ዚ​ህም በሮች የሚ​ገባ ሕዝ​ብህ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች