Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 19:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ኤር​ም​ያ​ስም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትን​ቢት ሊና​ገር ወደ​ዚያ ልኮት ከነ​በ​ረው ስፍራ ከቶ​ፌት ተመ​ለሰ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አደ​ባ​ባይ ቆሞ ለሕ​ዝቡ ሁሉ እን​ዲህ አላ​ቸው፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ኤርምያስም እግዚአብሔር ትንቢት እንዲናገር ልኮት ከነበረበት ከቶፌት ተመልሶ፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አደባባይ በመቆም፣ ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አለ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ኤርምያስም ጌታ ትንቢት እንዲናገር ልኮት ከነበረበት ስፍራ ከቶፌት መጣ፥ በጌታም ቤት አደባባይ ቆሞ ለሕዝብ ሁሉ እንዲህ አለ፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ቃሉን እንድናገርበት ካዘዘኝ ከቶፌት ተመልሼ መጣሁ፤ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አደባባይም ቆሜ እንዲህ ብዬ ነገርኳቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ኤርምያስም እግዚአብሔር ትንቢት ሊናገር ወደዚያ ልኮት ከነበረው ስፍራ ከቶፌት መጣ፥ በእግዚአብሔርም ቤት አደባባይ ቆሞ ለሕዝብ ሁሉ፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 19:14
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ጉባኤ መካ​ከል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ በአ​ዲሱ አደ​ባ​ባይ ፊት ቆመ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይለ​ኛል፥ “ሂድ፤ የይ​ሁ​ዳም ነገ​ሥ​ታት በሚ​ገ​ቡ​በ​ትና በሚ​ወ​ጡ​በት በሕ​ዝ​ብህ ልጆች በር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በሮች ሁሉ ቁም።”


ይህ​ንም ቃል ነቢዩ ኤር​ም​ያስ ለይ​ሁዳ ሕዝብ ሁሉና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለተ​ቀ​መጡ ሁሉ እን​ዲህ ሲል ተና​ገረ፦


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ ቁም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ውስጥ ይሰ​ግዱ ዘንድ ለሚ​መ​ጡት ለይ​ሁዳ ከተ​ሞች ሁሉ ትነ​ግ​ራ​ቸው ዘንድ ያዘ​ዝ​ሁ​ህን ቃል ሁሉ ተና​ገ​ራ​ቸው፤ አን​ዲ​ትም ቃል አታ​ጕ​ድል።


ነቢዩ ኤር​ም​ያ​ስም በካ​ህ​ና​ቱና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በቆ​ሙት ሕዝብ ሁሉ ፊት ለሐ​ሰ​ተ​ኛው ነቢይ ለሐ​ና​ንያ ተና​ገረ።


“ሂዱ፤ ወደ ቤተ መቅ​ደ​ስም ግቡና ለሕ​ዝብ ይህን የሕ​ይ​ወት ቃል አስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች