Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 17:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 እኔን ፈጽሞ ብት​ሰሙ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በሰ​ን​በ​ትም ቀን በዚ​ህች ከተማ በሮች ሸክም ባታ​ገቡ፥ የሰ​ን​በ​ት​ንም ቀን ብት​ቀ​ድሱ፥ ሥራ​ንም ሁሉ ባት​ሠ​ሩ​ባት፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ነገር ግን በጥንቃቄ ብትታዘዙኝ ይላል እግዚአብሔር፤ በሰንበትም ቀን በዚህች ከተማ በሮች ሸክም ይዛችሁ ባትገቡ፣ የሰንበትንም ቀን ምንም ሳትሠሩ ብትቀድሱት፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 “ ‘እኔን ፈጽሞ ብትሰሙ፥ ይላል ጌታ፥ በሰንበትም ቀን በዚህች ከተማ በሮች ሸክም ባታስገቡ፥ የሰንበትንም ቀን ብትቀድሱ ሥራንም ሁሉ ባትሠሩበት፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 “‘እንግዲህ የሚያዳምጡኝ ከሆኑ እነዚህ ሕዝብ ትእዛዜን እንዲጠብቁ ንገራቸው፤ በሰንበት ቀን ምንም ዐይነት ሸክም ይዘው በከተማይቱ በሮች አይግቡ፤ ሰንበትን የተቀደሰ ቀን አድርገው ያክብሩ እንጂ በዚያን ቀን ምንም ሥራ አይሥሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 እኔን ፈጽሞ ብትሰሙ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በሰንበትም ቀን በዚህች ከተማ በሮች ሸክም ባታገቡ፥ የሰንበትንም ቀን ብትቀድሱ ሥራንም ሁሉ ባትሠሩበት፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 17:24
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እር​ሱም፥ “አንተ የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አጥ​ብ​ቀህ ብት​ሰማ፥ በፊ​ቱም መል​ካ​ምን ብታ​ደ​ርግ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ብታ​ደ​ምጥ፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ሁሉ ብት​ጠ​ብቅ፥ በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ላይ ያመ​ጣ​ሁ​ትን በሽታ አላ​ደ​ር​ስ​ብ​ህም፤ እኔ ፈዋ​ሽህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና” አለ።


“የሰ​ን​በ​ትን ቀን ትቀ​ድ​ሳት ዘንድ አስብ።


ሁለት ፈረ​ሰ​ኞ​ችን ሲጋ​ልቡ አየሁ፤ አንዱ በአ​ህያ ላይ፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም በግ​መል ላይ ተቀ​ምጦ ነበር፤ ድም​ፃ​ቸው ግን እንደ ብዙ​ዎች ፈረ​ሰ​ኞች ድምፅ ነበረ።”


ገን​ዘ​ብን እን​ጀራ ላይ​ደለ፥ የድ​ካ​ማ​ች​ሁ​ንም ዋጋ ለማ​ያ​ጠ​ግብ ነገር ለምን ትመ​ዝ​ና​ላ​ችሁ? አድ​ም​ጡኝ፤ በረ​ከ​ት​ንም ብሉ፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁም በበ​ረ​ከት ደስ ይበ​ለው።


ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም ቀድሱ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ በእ​ኔና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ምል​ክት ይሁኑ።


በሩቅም ያሉት መጥተው የእግዚአብሔርን መቅደስ ይሠራሉ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ። የአምላካችሁንም የእግዚአብሔርን ቃል አጥብቃችሁ ብትሰሙ ይህ ይሆናል።


“እና​ንተ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትወ​ድዱ ዘንድ፥ በፍ​ጹም ልባ​ችሁ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ሳ​ችሁ ታመ​ል​ኩት ዘንድ ዛሬ ለእ​ና​ንተ የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛ​ዜን ፈጽ​ማ​ችሁ ብት​ሰሙ፥


አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትወ​ድዱ ዘንድ፥ በመ​ን​ገ​ዱም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ እር​ሱ​ንም ትከ​ተሉ ዘንድ፥ ዛሬ ለእ​ና​ንተ የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛዝ ሁሉ ብት​ጠ​ብቁ ብታ​ደ​ር​ጉ​አ​ትም፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች