Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 17:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ራሳ​ች​ሁን ጠብቁ፥ በሰ​ን​በ​ትም ቀን ምንም ሸክም አት​ሸ​ከሙ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በሮች አታ​ግቡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በሰንበት ቀን ሸክም ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች እንዳታስገቡ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ጌታ እንዲህ ይላል፦ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፥ በሰንበትም ቀን ሸክም አትሸከሙ፥ በኢየሩሳሌምም በሮች አታስገቡ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ሕይወታችሁን ለማዳን እኔ የምሰጣችሁን ማስጠንቀቂያ ጠብቁ፤ ስለዚህ በሰንበት ቀን ምንም ዐይነት ሸክም ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም ቅጽር በሮች አትግቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፥ በሰንበትም ቀን ሸክም አትሸከሙ፥ በኢየሩሳሌምም በሮች አታግቡ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 17:21
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“የሰ​ን​በ​ትን ቀን ትቀ​ድ​ሳት ዘንድ አስብ።


ልብህን አጥብቀህ ጠብቅ፥ የሕይወት መገኛ ከእርሱ ነውና።


ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ በእ​ር​ሱም ጸንቶ የሚ​ኖር፥ ሰን​በ​ታ​ት​ንም የሚ​ጠ​ብ​ቅና የማ​ያ​ረ​ክስ፥ እጁ​ንም ክፋት ከማ​ድ​ረግ የሚ​ጠ​ብቅ ሰው ብፁዕ ነው።”


ፈቃ​ድ​ህን በተ​ቀ​ደ​ሰው ቀኔ ከማ​ድ​ረግ እግ​ር​ህን ከሰ​ን​በት ብት​መ​ልስ፥ ሰን​በ​ት​ንም ደስታ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ቀ​ደሰ ብታ​ደ​ር​ገው፥ ክፉ ሥራን ለመ​ሥ​ራት እግ​ር​ህን ባታ​ነሣ፥ በአ​ፍ​ህም ክፉ ነገ​ርን ባት​ና​ገር፥


አላቸውም “ምን እንድትሰሙ ተጠበቁ። በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ይሰፈርላችኋል፤ ለእናንተም ይጨመርላችኋል።


እን​ግ​ዲህ እን​ዴት እን​ደ​ም​ት​ሰሙ አስ​ተ​ውሉ፤ ላለው ይሰ​ጠ​ዋል፤ ከሌ​ለው ግን ያው ያለው የሚ​መ​ስ​ለው እንኳ ይወ​ሰ​ድ​በ​ታል።”


አሁ​ንም በገዛ ደሙ የዋ​ጃ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ትጠ​ብቁ ዘንድ መን​ፈስ ቅዱስ እና​ን​ተን ጳጳ​ሳት አድ​ርጎ ለሾ​መ​ባት ለመ​ን​ጋው ሁሉና ለራ​ሳ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ።


ልባ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ስት፥ ፈቀቅ እን​ዳ​ትሉ፥ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት እን​ዳ​ታ​መ​ልኩ፥ እን​ዳ​ት​ሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸ​ውም ተጠ​ን​ቀቁ።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኮ​ሬብ ተራራ በእ​ሳት መካ​ከል ሆኖ በተ​ና​ገ​ራ​ችሁ ቀን መል​ኩን ከቶ አላ​ያ​ች​ሁ​ምና ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን እጅግ ጠብቁ፤


ከእ​ና​ንተ ጋር የተ​ማ​ማ​ለ​ውን የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን እን​ዳ​ት​ረሱ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የከ​ለ​ከ​ለ​ውን፥ በማ​ና​ቸ​ውም ቅርጽ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን ምስል እን​ዳ​ታ​ደ​ርጉ እን​ግ​ዲህ ተጠ​ን​ቀቁ።


“ለራ​ስህ ዕወቅ፤ ሰው​ነ​ት​ህን ፈጽ​መህ ጠብቅ፤ ዐይ​ኖ​ችህ ያዩ​ትን ይህን ሁሉ ነገር አት​ርሳ፤ በሕ​ይ​ወ​ትህ ዘመን ሁሉ ከል​ቡ​ናህ አይ​ውጣ፤ ለል​ጆ​ች​ህና ለልጅ ልጆ​ች​ህም አስ​ተ​ም​ራ​ቸው።


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትወ​ድ​ዱት ዘንድ ለራ​ሳ​ችሁ እጅግ ተጠ​ን​ቀቁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች