Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 16:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 “ስለ​ዚህ እነሆ በዚህ ወራት አስ​ታ​ው​ቃ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እጄ​ንና ኀይ​ሌ​ንም አሳ​ያ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ስሜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆነ ያው​ቃሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 “ስለዚህ አስተምራቸዋለሁ፤ ኀይሌንና ታላቅነቴን፣ አሁን አስተምራቸዋለሁ፤ እነርሱም ስሜ እግዚአብሔር፣ እንደ ሆነ ያውቃሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 “ስለዚህ፥ እነሆ፥ አስታውቃቸዋለሁ፥ በዚህች ጊዜ እጄንና ኃይሌን አስታውቃቸዋለሁ፤ እነርሱም ስሜ ጌታ እንደሆነ ያውቃሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 “ስለዚህ ሕዝቦች በሙሉ ኀይሌንና ታላቅነቴን በማያዳግም ሁኔታ እንዲያውቁት አደርጋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር መሆኔንም ያረጋግጣሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ስለዚህ፥ እነሆ፥ አስታውቃቸዋለሁ፥ በዚህች ጊዜ እጄንና ኃይሌን አስታውቃቸዋለሁ፥ እነርሱም ስሜ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ያውቃሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 16:21
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍር​ድን ማድ​ረግ ያው​ቃል፤ ኀጢ​አ​ተ​ኛው በእ​ጆቹ ሥራ ተጠ​መደ።


እኔም የፈ​ር​ዖ​ንን ልብ አጸ​ና​ለሁ፤ እር​ሱም ከኋ​ላ​ቸው ይከ​ተ​ላ​ቸ​ዋል፤ እኔም በፈ​ር​ዖ​ንና በሠ​ራ​ዊቱ ሁሉ ላይ እከ​ብ​ራ​ለሁ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ሁሉ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።” እነ​ር​ሱም እን​ዲሁ አደ​ረጉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጦር​ነ​ትን ያጠ​ፋል፤ ስሙም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤


ለአ​ብ​ር​ሃ​ምም፥ ለይ​ስ​ሐ​ቅም፥ ለያ​ዕ​ቆ​ብም ሁሉን እን​ደ​ሚ​ችል አም​ላክ ተገ​ለ​ጥሁ፤ ነገር ግን ስሜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ታ​ወ​ቀ​ላ​ቸ​ውም ነበር።


እኔ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መድ​ኀ​ኒ​ትህ ነኝ፤ ግብ​ፅ​ንና ኢት​ዮ​ጵ​ያን ለአ​ንተ ቤዛ አድ​ርጌ፥ ሴዎ​ን​ንም ለአ​ንተ ፋንታ ሰጥ​ቻ​ለሁ።


“ስሙ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሆነ፥ ምድ​ርን የፈ​ጠ​ራት፥ የሠ​ራ​ትና ያጸ​ናት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦


ሕዝ​ቅ​ኤ​ልም ምል​ክት ይሆ​ና​ች​ኋል፤ እርሱ እንደ አደ​ረገ ሁሉ እና​ንተ ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ፤ ይህም በመጣ ጊዜ እኔ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


በዚያ ቀን አፍህ ላመ​ለ​ጠው ይከ​ፈ​ታል፤ አን​ተም ትና​ገ​ራ​ለህ፤ ከዚ​ያም ወዲያ ዲዳ አት​ሆ​ንም፤ ምል​ክ​ትም ትሆ​ና​ቸ​ዋ​ለህ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”


በሕ​ዝቤ በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ ኤዶ​ም​ያ​ስን እበ​ቀ​ላ​ለሁ፤ እንደ ቍጣ​ዬና እንደ መዓ​ቴም መጠን በኤ​ዶ​ም​ያስ ያደ​ር​ጋሉ፤ በቀ​ሌ​ንም ያው​ቃሉ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ሙታ​ኖ​ቻ​ች​ሁም በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ይወ​ድ​ቃሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


ሁሉን የሚ​ሠ​ራና የሚ​ያ​ቅ​ናና፥ ብር​ሃ​ኑን ወደ መስዕ የሚ​መ​ል​ሰው፥ ቀኑን እንደ ሌሊት የሚ​ያ​ጨ​ል​መው፥ የባ​ሕ​ሩ​ንም ውኃ ጠርቶ በም​ድር ፊት የሚ​ያ​ፈ​ስ​ሰው ስሙ ሁሉን የሚ​ችል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች