Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 16:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ስለ​ዚህ እነሆ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ያወጣ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ዳግ​መኛ የማ​ይ​ባ​ል​በት ዘመን ይመ​ጣል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “ስለዚህ ሰዎች፣ ‘እስራኤላውያንን ከግብጽ ምድር ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን’ ብለው ከእንግዲህ የማይምሉበት ዘመን ይመጣል” ይላል እግዚአብሔር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 “ስለዚህ፥ እነሆ፦ ‘የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ምድር ያወጣ በሕያው ጌታ እምላለሁ!’ ተብሎ ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ ‘የእስራኤልን ሕዝብ ከግብጽ ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን’ ብለው የማይምሉበት ጊዜ ይመጣል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ስለዚህ፥ እነሆ፦ የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ምድር ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን! ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 16:14
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እና​ንተ ግን እንደ ሰው ትሞ​ታ​ላ​ችሁ፥ ከአ​ለ​ቆ​ችም እንደ አንዱ ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ።


“ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት ያወ​ጣ​ሁህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ እኔ ነኝ፤


እነሆ በቍ​ጣ​ዬና በመ​ዓቴ፥ በታ​ላ​ቅም መቅ​ሠ​ፍቴ እነ​ር​ሱን ካሳ​ደ​ድ​ሁ​ባት ሀገር ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ​ዚ​ህም ስፍራ እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ተዘ​ል​ለ​ውም እን​ዲ​ኖሩ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤


ከግብጽ ምድር አውጥቼሃለሁ፥ ከባርነት ቤትም ተቤዥቼሃለሁ፥ በፊትህም ሙሴንና አሮንን ማርያምንም ልኬልህ ነበር።


አን​ተም በግ​ብፅ ምድር ባሪያ እንደ ነበ​ርህ፥ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚያ እን​ዳ​ዳ​ነህ ዐስብ፤ ስለ​ዚህ እኔ ዛሬ ይህን ነገር አዝ​ዝ​ሃ​ለሁ።


“ጠላ​ቶ​ች​ህን ለመ​ው​ጋት በወ​ጣህ ጊዜ፥ ፈረ​ሶ​ች​ንና ፈረ​ሰ​ኞ​ችን ሕዝ​ቡ​ንም ከአ​ንተ ይልቅ በዝ​ተው ባየህ ጊዜ፥ ከግ​ብፅ ሀገር ያወ​ጣህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና አት​ፍ​ራ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች