Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 10:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ እነሆ በም​ድ​ሪቱ የሚ​ኖ​ሩ​ትን በመ​ከራ አሰ​ና​ክ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ መቅ​ሠ​ፍ​ት​ሽም እን​ዲ​ያ​ገ​ኛ​ቸው አስ​ጨ​ን​ቃ​ቸ​ዋ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ “በዚህች ምድር የሚኖሩትን፣ አሁን ወደ ውጪ እወነጭፋቸዋለሁ፤ ጕዳቱ እንዲሰማቸው፣ መከራ አመጣባቸዋለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ጌታ እንዲህ ይላልና፦ “እነሆ፥ በምድሪቱ የሚኖሩትን እስኪሰማቸው ድረስ በዚህ ጊዜ እወነጭፋቸዋለሁ፥ አስጨንቃቸዋለሁም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በዚህ ጊዜ በዚህች አገር የሚኖሩትን ሰዎች አስወጣለሁ፤ እነርሱን አስጨንቄ እንዲማረኩ አደርጋለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ በምድሪቱ የሚኖሩትን እስኪሰማቸው ድረስ በዚህ ጊዜ እወነጭፋቸዋለሁ፥ አስጨንቃቸውማለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 10:18
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሚ​ያ​ሳ​ድ​ድ​ህና ነፍ​ስ​ህን የሚሻ ሰው ቢነሣ፥ የጌ​ታዬ ነፍስ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በሕ​ይ​ወት ማሰ​ሪያ የታ​ሰ​ረች ትሆ​ና​ለች፤ የጠ​ላ​ቶ​ችህ ነፍስ ግን በወ​ን​ጭፍ እን​ደ​ሚ​ወ​ነ​ጨፍ ትሁን።


ለባሪያዎቼስ ለነቢያት ያዘዝኋቸው ቃሎቼና ሥርዓቴ በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሱምን? እነርሱም ተመልሰው፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በመንገዳችንና በሥራችን መጠን ያደርግብን ዘንድ እንዳሰበ እንዲሁ አድርጎብናል አሉ።


እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ፤ ይህን ክፉ ነገር አደ​ር​ግ​ባ​ቸው ዘንድ መና​ገሬ ለከ​ንቱ አይ​ደ​ለም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ የል​ቡን ዐሳብ ሠርቶ እስ​ኪ​ፈ​ጽም ድረስ አይ​መ​ለ​ስም፤ በኋ​ለ​ኛ​ውም ዘመን ያው​ቁ​ታል።


ስለ​ዚህ ከዚች ምድር እና​ን​ተና አባ​ቶ​ቻ​ችሁ ወደ አላ​ወ​ቃ​ች​ኋት ምድር እጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በዚ​ያም ምሕ​ረ​ትን ለማ​ያ​ደ​ር​ጉ​ላ​ችሁ ሌሎች አማ​ል​ክት ቀንና ሌሊት ታገ​ለ​ግ​ላ​ላ​ችሁ።”


በሀ​ገ​ርህ ሁሉ ያሉ፥ ትታ​መ​ን​ባ​ቸው የነ​በሩ፥ የረ​ዘሙ፥ የጸ​ኑም ቅጥ​ሮች እስ​ኪ​ፈ​ርሱ ድረስ፥ በከ​ተ​ሞ​ችህ ሁሉ ያጠ​ፋ​ሃል፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ጠህ ምድር ሁሉ፥ በደ​ጆች ሁሉ ያስ​ጨ​ን​ቅ​ሃል።


አን​ተ​ንም፥ የወ​ለ​ደ​ች​ህን እና​ት​ህ​ንም ወዳ​ል​ተ​ወ​ለ​ዳ​ች​ሁ​ባት ወደ ሌላ ሀገር እጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በዚ​ያም ትሞ​ታ​ላ​ችሁ።


በእግዚአብሔርም ላይ ኃጢአት ሠርተዋልና እንደ ዕውር እስኪሄዱ ድረስ ሰዎችን አስጨንቃለሁ፣ ደማቸውም እንደ ትቢያ፥ ሥጋቸውም እንደ ጕድፍ ይፈስሳል።


እነሆ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኀ​ይል ወር​ውሮ ይጥ​ል​ሃል፤ ያጠ​ፋ​ሃ​ልም፤ ልብ​ስ​ህ​ንና የክ​ብር አክ​ሊ​ል​ህ​ንም ይገ​ፍ​ሃል፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች