Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ያዕቆብ 4:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ትመኛላችሁ ለእናንተም አይሆንም፤ ትገድላላችሁ በብርቱም ትፈልጋላችሁ፥ ልታገኙም አትችሉም፤ ትጣላላችሁ ትዋጉማላችሁ ነገር ግን አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ትመኛላችሁ፤ ነገር ግን አታገኙም። ትገድላላችሁ፤ በብርቱም ትመኛላችሁ፤ ልታገኙም አትችሉም። ትጣላላችሁ፤ ትዋጋላችሁ፤ አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ትመኛላችሁ፤ ነገር ግን አታገኙም፤ ስለዚህ ትገድላላችሁ። በብርቱም ትመኛላችሁ፤ ልታገኙም አትችሉም፤ ስለዚህ ትጣላላችሁ፤ ትዋጋላችሁ። ስለማትለምኑ የምትፈልጉትን አታገኙም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 አንድን ነገር ለማግኘት ትመኛላችሁ፤ ግን አታገኙም፤ ስለዚህ ሰውን ትገድላላችሁ። ስለማትጸልዩም የምትፈልጉትን ነገር አታገኙም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ትመኛላችሁ ለእናንተም አይሆንም፤ ትገድላላችሁ በብርቱም ትፈልጋላችሁ፥ ልታገኙም አትችሉም፤ ትጣላላችሁ ትዋጉማላችሁ ነገር ግን አትለምኑምና ለእናንተ አይሆንም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ያዕቆብ 4:2
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይህ ካል​ሆነ ነገ በዚህ ጊዜ አገ​ል​ጋ​ዮቼን እል​ክ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ቤት​ህ​ንም፥ የአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህ​ንም ቤቶች ይበ​ረ​ብ​ራሉ፤ ለዐ​ይ​ና​ቸው ደስ ያሰ​ኛ​ቸ​ውን ሁሉና በእ​ጃ​ቸው የዳ​ሰ​ሱ​ት​ንም ሁሉ ይወ​ስ​ዳሉ።”


ይህ መንገድ ኀጢአትን የሚፈጽሙ ሁሉ ነው። ቅሚያ ነፍሳቸውን ታጠፋለች።


አንድ ሰው ብቻ​ውን አለ፥ ሁለ​ተ​ኛም የለ​ውም፥ ልጅም ሆነ ወን​ድም የለ​ውም፤ ለድ​ካሙ ግን መጨ​ረሻ የለ​ውም፥ ዐይ​ኖ​ቹም ከባ​ለ​ጠ​ግ​ነት አይ​ጠ​ግ​ቡም። ለማን እደ​ክ​ማ​ለሁ? ሰው​ነ​ቴ​ንስ ከደ​ስታ ለምን እነ​ፍ​ጋ​ታ​ለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር፥ ክፉም ጥረት ነው።


አካ​ዝም፥ “አል​ለ​ም​ንም፤ አም​ላኬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አል​ፈ​ታ​ተ​ንም” አለ።


እርሱ አታላይና ኵሩ ሰው ነው፣ በስፍራው ዐርፎ አይቀመጥም፣ ስስቱን እንደ ሲኦል ያሰፋል፥ እርሱም እንደ ሞት አይጠግብም፣ አሕዛብንም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበስባል፥ ወገኖቹንም ሁሉ ወደ እርሱ ያከማቻል።


እስ​ካ​ሁን ምንም በስሜ አል​ለ​መ​ና​ች​ሁም፤ ደስ​ታ​ችሁ ፍጹም ይሆን ዘንድ ለምኑ፤ ታገ​ኙ​ማ​ላ​ችሁ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስጦ​ታና ውኃ አጠ​ጪኝ ብሎ የሚ​ለ​ም​ንሽ ማን እንደ ሆነ ብታ​ው​ቂስ አንቺ ደግሞ በለ​መ​ን​ሺው ነበር፤ እር​ሱም የሕ​ይ​ወ​ትን ውኃ በሰ​ጠሽ ነበር” ብሎ መለ​ሰ​ላት።


ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፤ ለእርሱም ይሰጠዋል።


ጻድቁን ኰንናችሁታል፤ ገድላችሁትማል፤ እናንተን አይቃወምም።


ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው፥ ነፍሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች