Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሆሴዕ 7:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ሲሄ​ዱም አሽ​ክ​ላ​ዬን እዘ​ረ​ጋ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እንደ ሰማይ ወፎ​ችም አወ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ መከ​ራ​ቸ​ውን ሲሰሙ እገ​ሥ​ጻ​ቸ​ዋ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ሲበርሩ፣ መረቤን በላያቸው እዘረጋለሁ፤ እንደ ሰማይ ወፎችም ጐትቼ አወርዳቸዋለሁ። ስለ ክፉ ሥራቸውም፣ በጉባኤ መካከል እቀጣቸዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በመሄድ ላይ ሳሉ መረቤን በላያቸው እዘረጋለሁ፤ እንደ ሰማይ ወፎች አወርዳቸዋለሁ፤ በጉባኤያቸው ላይ እንደተላለፈው እገሥጻቸዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በሚዘዋወሩበት ቦታ ሁሉ ወጥመዴን ዘርግቼ እንደ ወፍ እይዛቸዋለሁ፤ ስለ ሠሩትም ክፉ ሥራ እቀጣቸዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ሲሄዱ አሽክላዬን እዘረጋባቸዋለሁ፥ እንደ ሰማይ ወፎች አወርዳቸዋለሁ፥ መከራቸውን ሲሰሙ እገሥጻቸዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሆሴዕ 7:12
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አወ​ከኝ፥ መዓ​ቱ​ንም በእኔ ላይ እንደ አበዛ ዕወቁ።


ሰውም ጊዜ​ውን አያ​ው​ቅም፤ በክፉ መረብ እንደ ተጠ​መዱ ዓሣ​ዎች ፥ በወ​ጥ​መ​ድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እን​ዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድ​ን​ገት ሲወ​ድ​ቅ​ባ​ቸው ይጠ​መ​ዳሉ።


“እነሆ፥ ብዙ ዓሣ አጥ​ማ​ጆ​ችን እል​ካ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እነ​ር​ሱም ያጠ​ም​ዱ​አ​ቸ​ዋል፤ ከዚ​ያም በኋላ ብዙ አድ​ዳ​ኞ​ችን እል​ካ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ከየ​ተ​ራ​ራ​ውና ከየ​ኮ​ረ​ብ​ታው ሁሉ ከየ​ድ​ን​ጋ​ዩም ስን​ጣቂ ውስጥ ያድ​ድ​ኑ​አ​ቸ​ዋል።


በማ​ለ​ዳም ባሪ​ያ​ዎ​ችን ነቢ​ያ​ትን ሁሉ ላክ​ሁ​ባ​ቸው፤ የጠ​ላ​ሁ​ት​ንም ርኩስ ነገር አታ​ድ​ርጉ ብዬ ላክ​ሁ​ባ​ቸው።


መረ​ቤ​ንም በእ​ርሱ ላይ እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ በወ​ጥ​መ​ዴም ይያ​ዛል፤ ወደ ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም ምድር ወደ ባቢ​ሎን አመ​ጣ​ዋ​ለሁ፤ ሆኖም አያ​ያ​ትም፤ በዚ​ያም ይሞ​ታል።


መረ​ቤ​ንም በእ​ርሱ ላይ እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ በወ​ጥ​መ​ድም ይያ​ዛል፤ ወደ ባቢ​ሎ​ንም አመ​ጣ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ኔም ላይ ስላ​ደ​ረ​ገው ዐመፅ በዚያ ከእ​ርሱ ጋር እፋ​ረ​ዳ​ለሁ።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በብዙ አሕ​ዛብ ጉባኤ መረ​ቤን እዘ​ረ​ጋ​ብ​ሃ​ለሁ፤ በመ​ረ​ቤም አወ​ጣ​ሃ​ለሁ።


ኤፍ​ሬም በዘ​ለፋ ቀን ለጥ​ፋት ይሆ​ናል፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ነገ​ዶች የታ​መ​ነ​ውን ነገር አሳ​የሁ።


እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና፤ ንስሓም ግባ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች