Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሆሴዕ 5:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ዲቃ​ሎ​ችን ልጆች ወል​ደ​ዋ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከድ​ተ​ዋል፤ አሁ​ንም ኵብ​ኵባ እነ​ር​ሱ​ንና ርስ​ታ​ቸ​ውን ይበ​ላ​ቸ​ዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ለእግዚአብሔር ታማኞች አልሆኑም፤ ዲቃሎች ወልደዋልና፤ ስለዚህ የወር መባቻ በዓላቸው፤ እነርሱንና ዕርሻቸውን ያጠፋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ዲቃሎችን ልጆች ወልደዋልና ጌታን አታልለዋል፤ አሁን ደግሞ እነርሱን ከርስታቸው ጋር የወሩ መባቻ ይበላቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እነርሱ ራሳቸው ጣዖት አምላኪዎች ስለ ሆኑ ለእግዚአብሔር ታማኞች ሆነው አልተገኙም። ልጆቻቸውም እንደ ጣዖት ልጆች ተቆጥረዋል፤ ስለዚህ በዚህ ወር መባቻ እነርሱም ምድራቸውም አብረው ይጠፋሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ዲቃሎችን ልጆች ወልደዋልና እግዚአብሔርን ወንጅለዋል፥ አሁንም አንድ ወር እነርሱንና ርስታቸውን ይበላቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሆሴዕ 5:7
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ለመ​ን​ግ​ሥ​ትህ ክብር ይገ​ባል” ይላሉ፥ ኀይ​ል​ህ​ንም ይነ​ጋ​ገ​ራሉ፥


የቸ​ር​ነ​ት​ህን ብዛት መታ​ሰ​ቢያ ይና​ገ​ራሉ፥ በጽ​ድ​ቅ​ህም ሐሤ​ትን ያደ​ር​ጋሉ።


መባ​ቻ​ች​ሁ​ንና በዓ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ነፍሴ ጠል​ታ​ለች፤ አስ​ጸ​ያፊ ሆና​ች​ሁ​ብ​ኛል፤ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁ​ንም ይቅር አል​ልም።


አላ​ወ​ቅ​ህም፤ አላ​ስ​ተ​ዋ​ል​ህም፤ ጆሮ​ህን ከጥ​ንት አል​ከ​ፈ​ት​ሁ​ል​ህም፤ አንተ ፈጽሞ ወን​ጀ​ለኛ እንደ ሆንህ፥ ከማ​ኅ​ፀ​ንም ጀም​ረህ ተላ​ላፊ ተብ​ለህ እንደ ተጠ​ራህ ዐው​ቄ​አ​ለ​ሁና።


በድ​ለ​ናል፤ ዋሽ​ተ​ና​ልም፤ አም​ላ​ካ​ች​ን​ንም መከ​ተል ትተ​ናል፤ ዐመ​ፃን ተና​ግ​ረ​ናል፤ ከድ​ተ​ን​ሃ​ልም፤ የኀ​ጢ​አ​ት​ንም ቃል ፀን​ሰን፤ ከልብ አው​ጥ​ተ​ናል።


ሚስት ባል​ዋን እን​ደ​ም​ት​ከዳ እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ከዱኝ” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


የእ​ስ​ራ​ኤል ቤትና የይ​ሁዳ ቤት በእኔ ላይ እጅግ ወን​ጅ​ለ​ዋል” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ስለ​ዚህ በላ​ቸው፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የም​ና​ገ​ረው ቃል ይፈ​ጸ​ማል እንጂ ከቃሌ ሁሉ ደግሞ የሚ​ዘ​ገይ የለም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ደስ​ታ​ዋ​ንም ሁሉ፥ በዓ​ላ​ቶ​ች​ዋ​ንም፥ መባ​ቻ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ ሰን​በ​ቶ​ች​ዋ​ንም፥ ሥር​ዐ​ቶ​ች​ዋ​ንም ሁሉ አስ​ቀ​ራ​ለሁ።


የዝ​ሙት ልጆች ናቸ​ውና ልጆ​ች​ዋን ይቅር አል​ላ​ቸ​ውም።


እነ​ርሱ ግን ቃል ኪዳ​ንን እን​ደ​ሚ​ያ​ፈ​ርስ ሰው ሆኑ፤ በዚ​ያም ላይ ከዱኝ።


ከእኔ ፈቀቅ ብለ​ዋ​ልና ወዮ​ላ​ቸው! እኔ​ንም ስለ በደሉ ደን​ግ​ጠ​ዋል! እኔ ታደ​ግ​ኋ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን በሐ​ሰት ተና​ገ​ሩ​ብኝ።


በአንድ ወርም ሦስቱን እረኞች አጠፋሁ፣ ነፍሴም ተሰቀቀቻቸው፥ ነፍሳቸውም ደግሞ እኔን ጠላች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች