ሆሴዕ 4:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 ከነዓናውያንንም መረጣቸው፤ ፈጽመውም አመነዘሩ፤ በክፋታቸውም ውርደትን መረጡ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 መጠጣቸው ባለቀ ጊዜ እንኳ፣ ዘማዊነታቸውን አያቆሙም፤ ገዦቻቸውም ነውርን አጥብቀው ይወድዳሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 ስካራቸውን ፈጽመዋል፥ ለምንዝርናም ራሳቸውን ፍጹም አስገዝተዋል፤ ከክብራቸው ይልቅ ውርደታቸውን እጅግ ወድደዋል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 ብዙ የወይን ጠጅ ከጠጡ በኋላ የዝሙት ሥራቸውን ይቀጥላሉ፤ አለቆቻቸውም አሳፋሪ ነገሮችን ማድረግ አጥብቀው ይወዳሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 ስካርን ፈጽመዋል፥ ግልሙትናንም አብዝተዋል፥ አለቆችዋም ነውርን እጅግ ወደዱ። ምዕራፉን ተመልከት |