Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 9:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኖኅን፥ “በእ​ኔና በም​ድር ላይ በሚ​ኖር፥ ሥጋ ባለው ሁሉ መካ​ከል ያጸ​ና​ሁት የቃል ኪዳን ምል​ክት ይህ ነው” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ስለዚህ እግዚአብሔር ኖኅን፣ “ይህ በእኔና በምድር ላይ በሚኖሩ ሕያዋን ሁሉ መካከል የገባሁት ኪዳን ምልክት ነው” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እግዚአብሔርም ኖኅን፦ “ይህ በእኔና በምድር ላይ በሚኖሩ ሕይወት ባላቸው ፍጥረቶች መካከል ያቆምሁት የቃል ኪዳን ምልክት ነው” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እግዚአብሔርም ኖኅን እንዲህ አለው፦ “ይህ ቀስት በምድር ላይ በእኔና ሕይወት ባላቸው ፍጥረቶች ሁሉ መካከል የገባሁትን ቃል ኪዳን የሚያስታውስ ምልክት ነው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እግዚአብሔርም ኖኅን፥ በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥግ ባለው ሁሉ መካከል ያቆምሁት የቃል ኪዳን ምልክት ይህ ነው አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 9:17
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ለኖኅ አለው፥ “በእ​ኔና በእ​ና​ንተ መካ​ከል፥ ከእ​ና​ን​ተም ጋር ባለው በሕ​ያው ነፍስ ሁሉ መካ​ከል፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ትው​ልድ የማ​ደ​ር​ገው የቃል ኪዳኔ ምል​ክት ይህ ነው፤


ቀስ​ቴም በደ​መና ትሆ​ና​ለች፤ በእ​ኔና በም​ድር መካ​ከል፥ በም​ድር ላይ በሚ​ኖር ሥጋ ባለው በሕ​ያው ነፍስ ሁሉ መካ​ከል ያለ​ውን የዘ​ለ​ዓ​ለም ቃል ኪዳን ለማ​ሰብ አያ​ታ​ለሁ።”


ከመ​ር​ከብ የወ​ጡት የኖኅ ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ሴም፥ ካም፥ ያፌት፤ ካምም የከ​ነ​ዓን አባት ነው።


“እኔም እነሆ፥ ቃል ኪዳ​ኔን ከእ​ና​ንተ ጋር፥ ከእ​ና​ን​ተም በኋላ ከዘ​ራ​ችሁ ጋር አጸ​ና​ለሁ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች