Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 49:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 “ዮሴፍ የሚ​ያ​ድግ ልጅ ነው፤ ለእኔ በጣም የተ​ወ​ደደ የሚ​ቀ​ና​ል​ኝና የሚ​ያ​ድ​ግ​ልኝ ልጅ ነው፤ ወደ እኔ የሚ​መ​ለ​ስም ጐል​ማሳ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 “ዮሴፍ፤ ፍሬያማ የወይን ተክል፣ በምንጭ ዳር የተተከለ ወይን ነው። ሐረጎቹ ቅጥርን ያለብሳሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ዮሴፍ ትንሹ የፍሬ ዛፍ ነው፥ በምንጭ አጠገብ የሚያፈራ የፍሬ ዛፍ፥ አረጎቹ በቅጥር ላይ ያድጋሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 “ዮሴፍ፥ በውሃ ምንጭ አጠገብ ተተክሎ፥ ሐረጎቹ በግድግዳ ላይ እንደሚዘረጉ ፍሬያማ ዛፍ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ዮሴፍ ትንሹ የፍሬ ዛፍ ነው፥ በምንጭ አጠገብ የሚያፈራ የፍሬ ዛፍ አረጎቹ በቅጥር ላይ ያድጋሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 49:22
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሁ​ለ​ተ​ኛ​ው​ንም ስም ኤፍ​ሬም ብሎ ጠራው፤ እን​ዲህ ሲል፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ከ​ራዬ ሀገር አብ​ዝ​ቶ​ኛ​ልና።”


በግ​ብፅ ምድር የተ​ወ​ለ​ዱ​ለት የዮ​ሴ​ፍም ልጆች ሁለት ናቸው፤ ወደ ግብፅ የገ​ቡት የያ​ዕ​ቆብ ቤተ ሰዎች ሁሉ ሰባ ናቸው።


ከዚ​ህም ነገር በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ “እነሆ፥ አባ​ታ​ችን ደከመ” ብለው ለዮ​ሴፍ ነገ​ሩት፤ እር​ሱም ሁለ​ቱን ልጆ​ቹን ምና​ሴ​ንና ኤፍ​ሬ​ምን ይዞ ሄደ።


ያዕ​ቆ​ብም ባረ​ካ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “አባ​ቶች አብ​ር​ሃ​ምና ይስ​ሐቅ በፊቱ ደስ ያሰ​ኙት እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከታ​ና​ሽ​ነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን የመ​ገ​በኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥


ከከፉ ነገር ሁሉ የአ​ዳ​ነኝ መል​አክ እርሱ እነ​ዚ​ህን ብላ​ቴ​ኖች ይባ​ርክ፤ ስሜም፥ የአ​ባ​ቶች የአ​ብ​ር​ሃ​ምና የይ​ስ​ሐ​ቅም ስም በእ​ነ​ርሱ ይጠራ፤ በም​ድር ላይ ይብዙ፤ የብዙ ብዙም ይሁኑ፤”


አሁ​ንም እኔ ወደ አንተ ከመ​ም​ጣቴ በፊት በግ​ብፅ ምድር የተ​ወ​ለ​ዱ​ልህ ሁለቱ ልጆ​ችህ ለእኔ ይሁኑ፤ ኤፍ​ሬ​ምና ምናሴ ለእኔ እንደ ሮቤ​ልና እንደ ስም​ዖን ናቸው።


በም​ክ​ራ​ቸው የሰ​ደ​ቡት ጌቶች ሆኑ​በት፤ ቀስ​ተ​ኞ​ችም ወጉት፤


እስ​ራ​ኤል እን​ዲህ ይበል፥ “ከት​ን​ሽ​ነቴ ጀምሮ ሁል​ጊዜ ተሰ​ለ​ፉ​ብኝ፤


ኃጥ​ኣን በጀ​ር​ባዬ ላይ መቱኝ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም አበ​ዙ​አት።”


ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ሁህ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ነኝና፤ አፍ​ህን አስፋ፥ እሞ​ላ​ዋ​ለ​ሁም።


ከእ​ር​ስ​ዋም የጸ​ናች በትር ወጣች፤ ለገ​ዥ​ዎ​ችም በትር ሆነች፤ በዛ​ፎ​ችም መካ​ከል ቁመቷ ረዘመ፤ በቅ​ር​ን​ጫ​ፎ​ች​ዋም ርዝ​መቷ ታየ።


ከወ​ን​ድ​ሞቹ መካ​ከል ይለ​ያል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከም​ድረ በዳ የሚ​ያ​ቃ​ጥል ነፋ​ስን ያመ​ጣል፤ ሥሩን ያደ​ር​ቃል፤ ምን​ጩ​ንም ያነ​ጥ​ፋል፤ ምድ​ርን ያደ​ር​ቃል፤ የተ​ወ​ደዱ ዕቃ​ዎ​ች​ንም ሁሉ ያጠ​ፋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች