Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 48:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ዮሴ​ፍም አባቱ ቀኝ እጁን በኤ​ፍ​ሬም ራስ ላይ ጭኖ በአየ ጊዜ ከባድ ነገር ሆነ​በት፤ ዮሴ​ፍም የአ​ባ​ቱን እጅ በም​ናሴ ራስ ላይ ይጭ​ነው ዘንድ ከኤ​ፍ​ሬም ራስ ላይ አነ​ሣው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ዮሴፍ፣ አባቱ ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ላይ ማድረጉን ሲያይ ተከፋ፤ ከኤፍሬም ራስ ላይ አንሥቶ በምናሴ ራስ ላይ ለማኖር የአባቱን እጅ ያዘ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ዮሴፍም አባቱ ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ላይ ጭኖ ባየ ጊዜ አሳዘነው፥ የአባቱንም እጅ በምናሴ ራስ ላይ ይጭነው ዘንድ ከኤፍሬም ራስ ላይ አነሣው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ዮሴፍ አባቱ ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ማድረጉን ባየ ጊዜ ቅር ተሰኘ፤ ስለዚህ ከኤፍሬም ራስ ላይ አንሥቶ በምናሴ ራስ ላይ ለማኖር የአባቱን እጅ ያዘ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ዮሴፍም አባቱ ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ላይ ጭኖ ባየ ጊዜ አሳዘነው የአባቱንም እጅ በምናሴ ራስ ላይ ይጭነው ዘንድ ከኤፍሬም ራስ ላይ አነሣው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 48:17
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እስ​ራ​ኤ​ልም ቀኝ እጁን ዘር​ግቶ በኤ​ፍ​ሬም ራስ ላይ አኖ​ረው፤ እር​ሱም ታናሽ ነበረ፤ ግራ​ው​ንም በም​ናሴ ራስ ላይ አኖረ፤ እጆ​ቹ​ንም አስ​ተ​ላ​ለፈ።


ሳይ​ወ​ለዱ፥ ክፉና መል​ካም ሥራም ሳይ​ሠሩ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መም​ረጡ በምን እንደ ሆነ ይታ​ወቅ ዘንድ፥


እግዚአብሔር ያያልና፥ ደስም አያሰኘውምና፥ ቍጣውን ከእርሱ ይመልሳል።


ይህም ነገር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ሆነ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ መቅ​ሠ​ፍ​ትን አመጣ።


ዘን​በ​ሪም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረገ፤ ከእ​ር​ሱም አስ​ቀ​ድሞ ከነ​በ​ሩት ይልቅ እጅግ ከፋ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ፊቱን፥ የቁ​መ​ቱ​ንም ዘለ​ግታ አትይ፤ ሰው እን​ደ​ሚ​ያይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አያ​ይ​ምና ናቅ​ሁት፤ ሰው ፊትን ያያል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ልብን ያያል” አለው።


በለ​ዓ​ምም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መል​አክ፥ “በድ​ያ​ለሁ፤ አንተ በመ​ን​ገድ ላይ በፊቴ እንደ ቆም​ህ​ብኝ አላ​ወ​ቅ​ሁም፤ እን​ግ​ዲህ አሁን አት​ወ​ድድ እን​ደ​ሆነ እመ​ለ​ሳ​ለሁ” አለው።


ሕዝ​ቡም በክ​ፋት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አጕ​ረ​መ​ረሙ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰምቶ ተቈጣ፤ እሳ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በእ​ነ​ርሱ ላይ ነደ​ደች፤ ከሰ​ፈ​ሩም አን​ዱን ወገን በላች።


ይህም ሥራው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ክፉ ሆነ​በት፤ እን​ዲህ አድ​ር​ጎ​አ​ልና እር​ሱ​ንም ደግሞ ቀሠ​ፈው።


የከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም ሴቶች ልጆች በአ​ባቱ በይ​ስ​ሐቅ ፊት የተ​ጠሉ እንደ ሆኑ ዔሳው በአየ ጊዜ፥


ዮሴ​ፍም አባ​ቱን፥ “አባቴ ሆይ፥ እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ በኵሩ ይህ ነውና ቀኝ​ህን በራሱ ላይ አድ​ርግ” አለው።


የም​ናሴ ልጆች ነገድ ድን​በር ይህ ነው፤ የዮ​ሴፍ በኵር እርሱ ነውና። የም​ና​ሴም በኵር የገ​ለ​ዓድ አባት ማኪር ብርቱ ተዋጊ ስለ ነበረ ገለ​ዓ​ድ​ንና ባሳ​ንን ወረሰ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች