Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 47:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ዮሴ​ፍም ለአ​ባ​ቱና ለወ​ን​ድ​ሞቹ፥ ለአ​ባ​ቱም ቤተ ሰዎች ሁሉ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው እየ​ሰ​ፈረ እህ​ልን ለም​ግብ ይሰ​ጣ​ቸው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ዮሴፍም ለአባቱ፣ ለወንድሞቹና ለመላው የአባቱ ቤተ ሰዎች በልጆቻቸው ቍጥር ልክ ቀለብ እንዲሰፈርላቸው አደረገ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ዮሴፍም ለአባቱና ለወንድሞቹ ለአባቱም ቤተ ሰዎች ሁሉ እንደ ልጆቻቸው መጠን እህል ሰጣቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ዮሴፍ ለአባቱና ለወንድሞቹ በልጆቻቸው ቊጥር ልክ እህል ይሰጣቸው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ዮሴፍም ለአባቱና ለወንድሞቹ ለአባቱም ቤተስዎች ሁሉ እንደ ልጆቻቸው መጠን እህል ሰጣቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 47:12
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚ​ያም አን​ተና የቤ​ትህ ሰዎች የአ​ንተ የሆ​ነው ሁሉ እን​ዳ​ት​ቸ​ገሩ እመ​ግ​ብ​ሃ​ለሁ፤ የራቡ ዘመን ገና አም​ስት ዓመት ቀር​ቶ​አ​ልና፤


ነገር ግን ለእርሱ ስለ ሆኑት ይልቁንም ስለ ቤተ ሰዎቹ የማያስብ ማንም ቢሆን፥ ሃይማኖትን የካደ ከማያምንም ሰው ይልቅ የሚከፋ ነው።


ማንም ባልቴት ግን ልጆች ወይም የልጅ ልጆች ቢኖሩአት፥ እነርሱ አስቀድመው ለገዛ ቤተ ሰዎቻቸው እግዚአብሔርን መምሰል ያሳዩ ዘንድ፥ ለወላጆቻቸውም ብድራትን ይመልሱላቸው ዘንድ ይማሩ፤ ይህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና የተወደደ ነውና።


ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው፥ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል።


ነገር ግን ሞግዚት የራስዋን ልጆች እንደምትከባከብ፥ በመካከላችሁ የዋሆች ሆንን፤


ከሰባትም ወንዶች ልጆች ይልቅ ለአንቺ ከምትሻል ከምትወድድሽ ምራት ተወልዶአልና ሰውነትሽን ያሳድሰዋል፥ በእርጅናሽም ይመግብሻል አሉአት።


“አባ​ት​ህ​ንና እና​ት​ህን አክ​ብር፤ መል​ካም እን​ዲ​ሆ​ን​ልህ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ በሚ​ሰ​ጥህ ምድ​ርም ዕድ​ሜህ እን​ዲ​ረ​ዝም።


በመ​ከ​ርም ጊዜ ፍሬ​ውን ከአ​ም​ስት እጅ አን​ዱን እጅ ለፈ​ር​ዖን ስጡ፤ አራ​ቱም እጅ ለእ​ና​ንተ ለራ​ሳ​ችሁ፥ ለእ​ር​ሻው ዘርና ለእ​ና​ንተ ምግብ፥ ለቤተ ሰባ​ች​ሁም ሁሉ ሲሳይ ይሁን።”


ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ ከግ​ብፅ ዳርቻ አን​ሥቶ እስከ ሌላው ዳር​ቻዋ ድረስ አገ​ል​ጋ​ዮች አደ​ረ​ጋ​ቸው።


ዮሴ​ፍም ገባ፤ ለፈ​ር​ዖ​ንም እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “አባ​ቴና ወን​ድ​ሞች በጎ​ቻ​ቸ​ውም፥ ላሞ​ቻ​ቸ​ውም፥ ያላ​ቸ​ውም ሁሉ ከከ​ነ​ዓን ምድር መጡ፤ እነ​ር​ሱም እነሆ፥ ወደ ጌሤም ምድር ደረሱ።”


አሁ​ንም አት​ፍሩ፤ እኔ እና​ን​ተ​ንና ቤተ ሰቦ​ቻ​ች​ሁን እመ​ግ​ባ​ች​ኋ​ለሁ።” አጽ​ና​ና​ቸ​ውም፤ በል​ባ​ቸው የሚ​ገባ ነገ​ርም ነገ​ራ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በም​ድር ላይ እን​ድ​ት​ድ​ኑና እን​ድ​ት​ተ​ርፉ እመ​ግ​ባ​ችሁ ዘንድ ከእ​ና​ንተ በፊት ላከኝ።


በዐ​ረብ በኩል በጌ​ሤም ምድ​ርም ትቀ​መ​ጣ​ለህ፤ ወደ እኔም ትቀ​ር​ባ​ለህ። አን​ተና ልጆ​ችህ የል​ጆ​ች​ህም ልጆች፥ በጎ​ች​ህና ላሞ​ችህ፥ የአ​ንተ የሆ​ነው ሁሉ፥


የአ​ባ​ቱ​ንም ቤት ክብር ሁሉ፥ ልጆ​ቹ​ንም፥ የልጅ ልጆ​ቹ​ንም፥ ከጽዋ ዕቃ ጀምሮ እስከ ማድጋ ዕቃ ድረስ፥ ታና​ና​ሹ​ንና ታላ​ላ​ቁን ሁሉ ይሰ​ቅ​ሉ​በ​ታል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች