ዘፍጥረት 45:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 እነሆ፥ ይህ ሁለቱ ዓመት በምድር ላይ ራብ የሆነበት ነውና፤ የማይታረስበትና የማይታጨድበት አምስት ዓመት ገና አለ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 በምድር ላይ ራብ ከገባ ይኸው ሁለት ዓመት ሆነ፤ ከዚህ በኋላም የማይታረስባቸውና ሰብል የማይሰበሰብባቸው ዐምስት ዓመታት ገና አሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ይህ በምድር ላይ ሁለት ዓመት ራብ የሆነበት ነው፥ ገና የማይታረስበትና የማይታጨድበት አምስት ዓመት ይመጣል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 በምድር ላይ ራብ ከገባ ሁለተኛ ዓመቱን ይዞአል፤ ሰዎች አርሰው መከር መሰብሰብ የማይችሉባቸው አምስት ዓመቶች ገና ይመጣሉ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ይህ ሁለቱ ዓመት በምድር ላይ ራብ የሆነበት ነውና የማይታረስበትና የማይታጨድበት አምስት ዓመት ገና ቀረ። ምዕራፉን ተመልከት |