Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 43:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ጌታ ሆይ፥ እን​ማ​ል​ድ​ሃ​ለን፤ ቀድሞ እህ​ልን ልን​ሸ​ምት ወር​ደን ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 “እንዲህም አሉት፤ ጌታችን ሆይ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ እህል ለመሸመት ወደዚህ መጥተን ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 እንዲህም አሉት፦ “ለመጀመሪያ ጊዜ እህል ለመሸመት ወደዚህ መጥተን ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 “ጌታዬ ከዚህ በፊት እህል ለመሸመት ወደዚህ መጥተን ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ጌታዬም ሆይ ቀድሞ እህልን ልንሸምት ወርደን ነበር

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 43:20
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነ​ር​ሱም አሉት፥ “ጌታ ሆይ፥ አይ​ደ​ለም፤ ባሪ​ያ​ዎ​ች​ህስ ስንዴ ሊገዙ መጥ​ተ​ዋል፤


ከእ​ነ​ር​ሱም አንዱ በአ​ደ​ሩ​በት ስፍራ ለአ​ህ​ዮቹ ገፈ​ራን ይሰጥ ዘንድ ዓይ​በ​ቱን ፈታ፤ ብሩ​ንም በዓ​ይ​በቱ አፍ ተቋ​ጥሮ አገኘ።


የዮ​ሴ​ፍም ዐሥሩ ወን​ድ​ሞቹ እህ​ልን ከግ​ብፅ ይሸ​ምቱ ዘንድ ወረዱ፤


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዓይ​በ​ታ​ቸ​ውን በፈቱ ጊዜ እነሆ፥ ከእ​ነ​ርሱ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ብራ​ቸ​ውን በዓ​ይ​በ​ታ​ቸው ተቋ​ጥሮ አገ​ኙት፤ እነ​ር​ሱም አባ​ታ​ቸ​ውም የተ​ቋ​ጠረ ብራ​ቸ​ውን አይ​ተው ፈሩ።


ወደ ዮሴፍ ቤት አዛ​ዥም ቀረቡ፤ በቤ​ቱም ደጅ ተና​ገ​ሩት፤


እን​ዲ​ህም ሆነ፥ ወደ​ም​ና​ድ​ር​በ​ትም ስፍራ በደ​ረ​ስን ጊዜ ዓይ​በ​ታ​ች​ንን ከፈ​ትን፤ እነ​ሆም፥ የየ​አ​ን​ዳ​ንዱ ሰው ብር በየ​ዓ​ይ​በቱ አፍ ነበር፤ አሁ​ንም ብራ​ች​ንን በእ​ጃ​ችን እንደ ሚዛኑ መለ​ስ​ነው።


ይሁ​ዳም እን​ዲህ አለው፥ “የሀ​ገሩ ጌታ ያ ሰው፦ ‘ወን​ድ​ማ​ችሁ ከእ​ና​ንተ ጋር ከአ​ል​መጣ ፊቴን አታ​ዩም’ ብሎ በም​ስ​ክር ፊት አዳ​ኝ​ቶ​ብ​ናል።


እነ​ር​ሱም አሉ፥ “ያ ሰው ስለ እኛና ስለ ትው​ል​ዳ​ችን ፈጽሞ ጠየ​ቀን፤ እን​ዲ​ህም አለን፦ ‘ሽማ​ግ​ሌው አባ​ታ​ችሁ ገና በሕ​ይ​ወት ነው? ወን​ድ​ምስ አላ​ች​ሁን?’ እኛም እን​ደ​ዚሁ እንደ ጠየ​ቀን መለ​ስ​ን​ለት፤ በውኑ፦ ‘ወን​ድ​ማ​ች​ሁን አምጡ’ እን​ዲ​ለን እና​ውቅ ነበ​ርን?”


አን​ደ​ኛ​ዪ​ቱም ሴት አለች፥ “ጌታዬ ሆይ! ስማኝ፥ እኔና ይህች ሴት በአ​ንድ ቤት እን​ኖ​ራ​ለን፤ በአ​ንድ ቤትም ወለ​ድን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች