Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 41:57 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

57 ሀገ​ሮ​ችም ሁሉ ከዮ​ሴፍ እህል ይገዙ ዘንድ ወደ ግብፅ ወጡ፤ በም​ድር ሁሉ ራብ እጅግ ጸንቶ ነበ​ርና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

57 ራቡ በመላው ዓለም ጸንቶ ስለ ነበር፣ የየአገሩ ሰዎች ሁሉ ከዮሴፍ ዘንድ እህል ለመሸመት ወደ ግብጽ ምድር መጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

57 ራቡ በመላው ዓለም ጸንቶ ስለ ነበር፥ የየአገሩ ሰዎች ሁሉ ከዮሴፍ ዘንድ እህል ለመሸመት ወደ ግብጽ ምድር መጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

57 በዓለም ላይ ራብ ጸንቶ ስለ ነበር የልዩ ልዩ አገር ሕዝቦች ከዮሴፍ እህል ለመግዛት ወደ ግብጽ አገር መጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

57 አገሮችም ሁሉ እህል ይገዙ ዘንድ ወደ ግብፅ ወደ ዮሴፍ መጡ በምድር ሁሉ ራብ እጅግ ጸንቶ ነበርና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 41:57
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ለእ​ህል ሸመታ ከመ​ጡት ጋር ገቡ፤ በከ​ነ​ዓን ሀገር ራብ ነበ​ርና።


በም​ድ​ርም ሁሉ ላይ ራብ ሆነ፤ ዮሴ​ፍም እህል ያለ​በ​ትን ጎተራ ሁሉ ከፍቶ ለግ​ብፅ ሰዎች ሁሉ ይሸጥ ነበር።


ዮሴ​ፍም እንደ ተና​ገረ ሰባቱ የራብ ዓመት መም​ጣት ጀመረ። በየ​ሀ​ገ​ሩም ሁሉ ራብ ሆነ፤ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ግን እህል ነበረ።


ከእ​ር​ስዋ እኛን ያወ​ጣ​ህ​ባት ምድር ሰዎች፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተስፋ ወደ ሰጣ​ቸው ምድር ያገ​ባ​ቸው ዘንድ አል​ቻ​ለ​ምና፥ ጠል​ቶ​አ​ቸ​ው​ማ​ልና ስለ​ዚህ በም​ድረ በዳ ሊገ​ድ​ላ​ቸው አወ​ጣ​ቸው እን​ዳ​ይሉ።


እና​ንተ በእኔ ላይ ክፉ መከ​ራ​ችሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እን​ዲ​መ​ገብ ለማ​ድ​ረግ ለእኔ መል​ካም መከረ።


ያዕ​ቆ​ብም በግ​ብፅ የሚ​ሸ​መት እህል እን​ዳለ ሰማ፤ ልጆ​ቹ​ንም፥ “ለምን ትተ​ክ​ዛ​ላ​ችሁ?” አላ​ቸው።


በም​ድ​ርም ራብ ሆነ፤ አብ​ራ​ምም በዚያ በእ​ን​ግ​ድ​ነት ይቀ​መጥ ዘንድ ወደ ግብፅ ወረደ፤ በም​ድር ራብ ጠንቶ ነበ​ረና።


ከዚ​ህም በኋላ ራብ በሀ​ገር ላይ ጸና።


ዮሴ​ፍም በግ​ብፅ ምድር ላይ ገዥ ነበረ፤ እር​ሱም ለም​ድር ሕዝብ ሁሉ እህል ይሸጥ ነበር፤ የዮ​ሴ​ፍም ወን​ድ​ሞች በመጡ ጊዜ በም​ድር ላይ በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ሰገ​ዱ​ለት።


ዮሴ​ፍም ከግ​ብፅ ምድ​ርና ከከ​ነ​ዓን ምድር በእ​ህል ሸመታ የተ​ገ​ኘ​ውን ብሩን ሁሉ አከ​ማቸ፤ ዮሴ​ፍም ብሩን ወደ ፈር​ዖን ቤት አስ​ገ​ባው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች