Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 41:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 አንተ በቤቴ ላይ ተሾም፤ ሕዝ​ቤም ሁሉ ለቃ​ልህ ይታ​ዘዝ፤ እኔም ከዙ​ፋኔ በቀር ከአ​ንተ የም​በ​ል​ጥ​በት የለም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 አንተ በቤተ መንግሥቴ የበላይ ትሆናለህ፤ ሕዝቤም ሁሉ ለሥልጣንህ ይገዛል፤ እኔ ከአንተ የምበልጠው በዙፋኔ ብቻ ይሆናል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 አንተ በቤተ መንግሥቴ የበላይ ትሆናለህ፤ ሕዝቤም ሁሉ ለሥልጣንህ ይገዛል፤ እኔ ከአንተ የምበልጠው በዙፋኔ ብቻ ይሆናል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 ስለዚህ አንተን በአገሬ ላይ አስተዳዳሪ አድርጌ እሾምሃለሁ፤ ሕዝቡም ሁሉ ይታዘዝሃል፤ በሥልጣንም ከእኔ በቀር የሚበልጥህ የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 አንተ በቤቴ ላይ ተሾምክ ሕዝቤም ሁሉ ለቃልህ ይታዘዝ እኔ በዙፋኔ ብቻ ከአንተ እበልጣለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 41:40
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከመ​ከ​ራ​ውም ሁሉ አዳ​ነው፤ በግ​ብፅ ንጉሥ በፈ​ር​ዖን ፊትም ሞገ​ስ​ንና ጥበ​ብን ሰጠው፤ በግ​ብ​ፅና በቤቱ ሁሉ ላይ ቢት​ወ​ደድ አድ​ርጎ ሾመው።


ነገርን የሚረዳ፥ በሥራውም ብልህ የሆነ ሰው፥ ወደ ነገሥታት ይቀርባል፤ በተዋረዱ ሰዎችም ፊት አይቆምም።


ጥበ​ብን አጽ​ኑ​አት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ይ​ቈጣ፥ እና​ን​ተም ከጽ​ድቅ መን​ገድ እን​ዳ​ት​ጠፉ፥ ቍጣው ፈጥና በነ​ደ​ደች ጊዜ፥ በእ​ርሱ የታ​መኑ ሁሉ ብፁ​ዓን ናቸው።


እን​ዲ​ህም ብለው ነገ​ሩት፥ “ልጅህ ዮሴፍ በሕ​ይ​ወቱ ነው፤ እር​ሱም በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ላይ ገዥ ሆኖ​አል።” ያዕ​ቆ​ብም ልቡ ደነ​ገጠ፤ አላ​መ​ና​ቸ​ው​ምም፤


ልቤ በስ​ውር ተታ​ልሎ እንደ ሆነ፥ በአ​ፌም ላይ እጄን አኑሬ ስሜ እንደ ሆነ፥


ሳሙ​ኤ​ልም የዘ​ይ​ቱን ቀንድ ወስዶ በራሱ ላይ አፈ​ሰ​ሰው፤ ሳመ​ውም፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “በሕ​ዝቡ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ትነ​ግሥ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀብ​ቶ​ሃል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሕዝብ ትገ​ዛ​ለህ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ካሉ ጠላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ ታድ​ና​ቸ​ዋ​ለህ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በር​ስቱ ላይ ትነ​ግሥ ዘንድ እንደ ቀባህ ምል​ክቱ ይህ ነው።


በዚህ ቤት ከእኔ የሚ​በ​ልጥ ሰው የለም፤ ሚስቱ ስለ​ሆ​ንሽ ከአ​ንቺ በቀር ያል​ሰ​ጠኝ ነገር የለም፤ እን​ዴት ይህን ትልቅ ክፉ ነገር አደ​ር​ጋ​ለሁ? በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዴት ኀጢ​አ​ትን እሠ​ራ​ለሁ?”


ይሁ​ዳም ወደ እርሱ ቀረበ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ በፊ​ትህ አን​ዲት ቃልን እን​ድ​ና​ገር እለ​ም​ና​ለሁ፤ እኔን አገ​ል​ጋ​ይ​ህን አት​ቈ​ጣኝ፤ አንተ ከፈ​ር​ዖን ቀጥ​ለህ ነህና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች