Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 41:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ የወ​ጡት እነ​ዚያ የከ​ሱና መልከ ክፉ​ዎቹ ሰባት ላሞች ሰባት ዓመ​ታት ናቸው፤ እነ​ዚ​ያም የሰ​ለ​ቱ​ትና ነፋስ የመ​ታ​ቸው ሰባቱ እሸ​ቶች እነ​ርሱ ራብ የሚ​ሆ​ን​ባ​ቸው ሰባት ዓመ​ታት ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ከእነርሱም በኋላ ዐጥንታቸው የወጣ አስከፊ መልክ ያላቸው ሰባት ላሞች፣ ሰባት ዓመታት ናቸው፤ እንደዚሁም ፍሬ አልባ የሆኑትና በምሥራቅ ነፋስ ተመትተው የደረቁት ሰባት የእሸት ዛላዎች ሰባት የራብ ዓመታት ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ከእነርሱም በኋላ ዐጥንታቸው የወጣ አስከፊ መልክ ያላቸው ሰባት ላሞች፥ ሰባት ዓመታት ናቸው፤ እንደዚሁም ፍሬ አልባ የሆኑትና በምሥራቅ ነፋስ ተመትተው የደረቁት ሰባት የእሸት ዛላዎች ሰባት የራብ ዓመታት ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ከእነርሱም በኋላ የወጡት ሰባት የከሱትና አስከፊዎቹ ላሞች ሰባት ዓመቶች ናቸው፤ እንዲሁም ሰባቱ የቀጨጩና በበረሓ ነፋስ ተመተው የሰለቱ የእሸት ዛላዎች ሰባት ዓመቶች ናቸው፤ የሁለቱም ትርጒም አንድ ነው፤ ይኸውም ሰባት የራብ ዓመቶች ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ከእነርሱም በኍላ የወጡት የከሱትና መልከ ክፋዎቹ ሰባት ላሞች ሰባት ዓመታት ናቸው፥ የሰለቱትና የምሥራቅ ነፋስ የመታቸው ሰባቱም እሽቶች እነርሱ ራብ የሚሆንባቸው ሰባት ዓመታት ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 41:27
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኤል​ሳ​ዕም ልጅ​ዋን ያስ​ነ​ሣ​ላ​ትን ሴት፥ “አንቺ ከቤተ ሰብሽ ጋር ተነ​ሥ​ተሽ ሂጂ፤ በም​ታ​ገ​ኚ​ውም ስፍራ ተቀ​መጪ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር ራብን ጠር​ቶ​አ​ልና፤ ሰባት ዓመ​ትም በም​ድር ላይ ይቆ​ያል” ብሎ ተና​ገ​ራት።


ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው እንደ ጋድ ነገር ወጣ።


ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ እነሆ፥ መል​ካ​ቸው የከፋ፥ ሥጋ​ቸ​ውም የከሳ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወ​ንዙ ወጡ፤ በእ​ነ​ዚ​ያም ላሞች አጠ​ገብ በወ​ንዙ ዳር ተሰ​ማ​ር​ተው ነበር።


እነ​ዚያ ሰባቱ መል​ካ​ካ​ሞች ላሞች ሰባት ዓመ​ታት ናቸው፤ እነ​ዚ​ያም ሰባቱ መል​ካ​ካ​ሞች እሸ​ቶች ሰባት ዓመ​ታት ናቸው፤ የፈ​ር​ዖን ሕልሙ አንድ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች