Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 4:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ቃየ​ልም ወን​ድ​ሙን አቤ​ልን፥ “ና ወደ ሜዳ እን​ሂድ” አለው። በሜ​ዳም ሳሉ ቃየል በወ​ን​ድሙ በአ​ቤል ላይ ተነ​ሣ​በት፤ ገደ​ለ​ውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ቃየንም ወንድሙን አቤልን፣ “እስኪ ና፤ ወደ መስኩ እንውጣ” አለው፤ በመስኩም ሳሉ፣ ቃየን ወንድሙን አቤልን አጠቃው፤ ገደለውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ቃየንም ወንድሙን አቤልን፥ “ና ወደ ሜዳ እንሂድ” አለው። በሜዳም ሳሉ፥ ቃየን በወንድሙ በአቤል ላይ ተነሣበት፥ ገደለውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ከዚህ በኋላ ቃየል ወንድሙን አቤልን “ና ወደ ሜዳ እንሂድ” አለው፤ ወደ ሜዳም በሄዱ ጊዜ ቃየል በጠላትነት ተነሥቶ ወንድሙን አቤልን ገደለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ቃየንም ወንድሙን አቤልን፤ ና ወደ ሜዳ እንሂድ አለው። በሜዳም ሳሉ ቃየን በወንድሙ በአቤል ላይ ተነሣበት፤ ገደለውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 4:8
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወዮላቸው! በቃየል መንገድ ሄደዋልና፤ ስለ ደመወዝም ለበለዓም ስሕተት ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል፤ በቆሬም መቃወም ጠፍተዋል።


ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቅ ደም ሁሉ ይደርስባችኋል።


ከአ​ቤል ደም ጀምሮ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውና በቤተ መቅ​ደሱ መካ​ከል እስከ ገደ​ሉት እስከ ዘካ​ር​ያስ ደም ድረስ እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ ከዚች ትው​ልድ ይፈ​ለ​ጋል።


ወንድ ልጅ አባቱን ይንቃልና፥ ሴት ልጅ በእናትዋ ላይ፥ ምራቲቱም በአማትዋ ላይ ትነሣለችና፥ የሰው ጠላቶች የቤቱ ሰዎች ናቸውና።


ለእ​ኔም ለአ​ገ​ል​ጋ​ይህ ሁለት ወን​ዶች ልጆች ነበ​ሩኝ፤ በሜ​ዳም ተጣሉ፤ የሚ​ገ​ላ​ግ​ላ​ቸ​ውም አል​ነ​በ​ረም፤ አን​ዱም ሌላ​ውን መትቶ ገደ​ለው።


ሰን​ባ​ላ​ጥና ጌሳም፥ “መጥ​ተህ በኦኖ ቈላ ውስጥ ባሉት መን​ደ​ሮች እን​ገ​ናኝ” ብለው ላኩ​ብኝ፤ ነገር ግን ክፉ ያደ​ር​ጉ​ብኝ ዘንድ ይመ​ክሩ ነበር።


አበ​ኔ​ርም ወደ ኬብ​ሮን በተ​መ​ለሰ ጊዜ ኢዮ​አብ በበር ውስጥ በቈ​ይታ ይና​ገ​ረው ዘንድ ወደ አጠ​ገቡ ወሰ​ደው፤ በዚ​ያም ለወ​ን​ድሙ ለአ​ሣ​ሄል ደም ተበ​ቅሎ ወገ​ቡን መታው፤ ሞተም።


የአ​ዲስ ኪዳ​ንም መካ​ከ​ለኛ ወደ​ሚ​ሆን ወደ ኢየ​ሱስ፥ ከአ​ቤ​ልም ደም ይልቅ የሚ​ሻ​ለ​ውን ወደ​ሚ​ና​ገር ወደ ተረ​ጨው ደሙ ደር​ሳ​ች​ኋል።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመን፥ መል​ካ​ም​ንም አድ​ርግ፥ በም​ድ​ርም ያሳ​ድ​ር​ሃል፥ በሀ​ብ​ት​ዋም ያሰ​ማ​ር​ሃል።


በዚ​ያን ጊዜ ፊትህ በን​ጹሕ ውኃ እንደ ታጠበ ያበ​ራል፥ መተ​ዳ​ደ​ፍ​ህ​ንም ታስ​ወ​ግ​ዳ​ለህ፥ አት​ፈ​ራ​ምም።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይሁ​ዳን፥ “በመ​ሳም የሰ​ውን ልጅ አሳ​ል​ፈህ ትሰ​ጠ​ዋ​ለ​ህን?” አለው።


አቤል ከቃ​ኤል ይልቅ የሚ​በ​ልጥ መሥ​ዋ​ዕ​ትን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ም​ነት አቀ​ረበ፤ በዚ​ህም ጻድቅ እንደ ሆነ ተመ​ሰ​ከ​ረ​ለት፤ ምስ​ክ​ሩም መሥ​ዋ​ዕ​ቱን በመ​ቀ​በል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው። በዚ​ህም ከሞተ በኋላ እንኳ ተና​ገረ።


አዳ​ምም ዳግ​መኛ ሚስ​ቱን ዐወ​ቃት፤ ፀነ​ሰ​ችም፤ ወንድ ልጅ​ንም ወለ​ደች። ስሙ​ንም ቃየል በገ​ደ​ለው በአ​ቤል ፈንታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሌላ ዘር ተክ​ቶ​ል​ኛል ስትል ሴት አለ​ችው።


ጥል ቢጣ​ላው፥ ወይም ሸምቆ አን​ዳች ነገር ቢጥ​ል​በት፥ ቢሞ​ትም፥


ኢዮ​ራ​ምም በአ​ባቱ መን​ግ​ሥት ላይ ተነ​ሥቶ በጸና ጊዜ ወን​ድ​ሞ​ቹን ሁሉ፥ ሌሎ​ች​ንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን መሳ​ፍ​ንት በሰ​ይፍ ገደለ።


ነገር ግን ሐሰት፥ ግዳ​ይና ስር​ቆት፥ ምን​ዝ​ር​ናም ምድ​ርን ሞል​ተ​ዋል፤ ደም​ንም ከደም ጋር ይቀ​ላ​ቅ​ላሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች