Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 4:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ሴትም ወንድ ልጅ ወለደ። ስሙ​ንም ሄኖስ አለው፤ እር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም መጥ​ራት የጀ​መረ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ለሴትም ደግሞ ወንድ ልጅ ተወለደለት፤ ስሙንም ሄኖስ አለው። በዚያም ዘመን ሰዎች የእግዚአብሔርን ስም መጥራት ጀመሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ሴትም ወንድ ልጅ ወለደ። ስሙንም ሄኖስ አለው፤ በዚያን ጊዜም የጌታ ስም በሰው መጠራት ተጀመረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ሤትም “ሄኖስ” የተባለውን ወንድ ልጅ ወለደ፤ ሰዎች የእግዚአብሔርን ስም መጥራት የጀመሩት በዚያን ጊዜ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ለሴት ደግሞ ወንድ ልጅ ተወለደስት፤ ስሙንም ሄኖስ አለው፤ በዚያን ጊዜም በእግዚአብሔር ስም መጠራት ተጀመረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 4:26
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እና​ን​ተም የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን ስም ጥሩ፤ እኔም የፈ​ጣ​ሪ​ዬን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም እጠ​ራ​ለሁ፤ ሰም​ቶም በእ​ሳት የሚ​መ​ልስ አም​ላክ፥ እርሱ አም​ላክ ይሁን።” ሕዝ​ቡም ሁሉ፥ “ይህ ነገር መል​ካም ነው” ብለው መለሱ።


በዚያን ጊዜም አሕዛብ ሁሉ አንድ ሆነው እግዚአብሔርን ያገለግሉት ዘንድ ስሙን እንዲጠሩ ንጹሕን ልሳን እመልስላቸዋለሁ።


እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም የሚ​ጠራ ሁሉ ይድ​ናል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገረ፥ በጽ​ዮን ተራ​ራና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይድ​ናሉ። ደግ​ሞም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጠ​ራ​ቸው፥ የም​ሥ​ራች የሚ​ሰ​በ​ክ​ላ​ቸው ይገ​ኛሉ።


ከዚ​ያም በቤ​ቴል ምሥ​ራቅ ወዳ​ለው ተራራ ወጣ፤ በዚ​ያም ቤቴ​ልን ወደ ምዕ​ራብ፥ ጋይን ወደ ምሥ​ራቅ አድ​ርጎ ድን​ኳ​ኑን ተከለ፤ በዚ​ያም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ው​ያን ሠራ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም ጠራ።


የሄ​ኖስ ልጅ፥ የሴት ልጅ፥ የአ​ዳም ልጅ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ።


በዚ​ያም ዘመን ይሁዳ ይድ​ናል፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ተዘ​ልላ ትቀ​መ​ጣ​ለች፤ የም​ት​ጠ​ራ​በ​ትም ስም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽድ​ቃ​ችን ተብሎ ነው።


በዚ​ያም ለአ​ም​ላኩ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ው​ያን ሠራ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም ጠራ፤ በዚ​ያም ድን​ኳን ተከለ፤ የይ​ስ​ሐ​ቅም ሎሌ​ዎች በዚያ ጕድ​ጓድ ማሱ።


በቆ​ሮ​ን​ቶስ ሀገር ላለች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ለከ​በ​ሩና ቅዱ​ሳን ለተ​ባሉ የእ​ነ​ር​ሱና የእኛ ጌታ የሆ​ነ​ውን የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ስም በየ​ስ​ፍ​ራው ለሚ​ጠሩ ሁሉ፥


“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም የሚ​ጠራ ሁሉ ይድ​ናል።”


በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም አንድ ዓመት አብ​ረው ተቀ​መጡ፤ ብዙ ሕዝ​ብ​ንም አስ​ተ​ማሩ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም መጀ​መ​ሪያ በአ​ን​ጾ​ኪያ ክር​ስ​ቲ​ያን ተብ​ለው ተጠሩ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም የሚ​ጠራ ሁሉ ይድ​ናል።


ከጥ​ንት እን​ዳ​ል​ገ​ዛ​ኸን ስም​ህም በእኛ ላይ እን​ዳ​ል​ተ​ጠራ ሆነ​ና​ልና።


እና​ንተ በእ​ስ​ራ​ኤል ስም የተ​ጠ​ራ​ችሁ፥ ከይ​ሁ​ዳም የወ​ጣ​ችሁ፥ በእ​ው​ነት ሳይ​ሆን፥ በጽ​ድ​ቅም ሳይ​ሆን እር​ሱን እየ​ጠ​ራ​ችሁ በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም የም​ት​ምሉ የያ​ዕ​ቆብ ቤት ሆይ፥ ይህን ስሙ፤


ይህ፦ እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ ይላል፤ ያም በያ​ዕ​ቆብ ስም ይጠ​ራል፤ ይህም፦ እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ ብሎ በእጁ ይጽ​ፋል፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ስም ይጠ​ራል።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች