Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 4:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ዓዳም ዮቤ​ልን ወለ​ደች፤ እር​ሱም በድ​ን​ኳን የሚ​ቀ​መ​ጡት የዘ​ላ​ኖች አባት ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ዓዳ ያባልን ወለደች፤ እርሱም በድንኳን ለሚኖሩ ከብት አርቢዎች አባት ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ዓዳም ያባልን ወለደች፥ እርሱም በድንኳን የሚቀመጡት የዘላኖች አባት ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ዓዳ ያባልን ወለደች፤ ያባልም ከብቶች እየጠበቁ በድንኳን ይኖሩ የነበሩት የዘላኖች ሰዎች አባት ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ዓዳም ያባልን ወለደች፤ እርሱም በድንኳን የሚቀመጡት የዘላኖች አባት ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 4:20
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በእ​ም​ነ​ትም ከሀ​ገሩ ወጥቶ ተስፋ በሰ​ጠው ሀገር እንደ ስደ​ተኛ በድ​ን​ኳን፥ ተስ​ፋ​ውን ከሚ​ወ​ር​ሱ​አት ከይ​ስ​ሐ​ቅና ከያ​ዕ​ቆብ ጋር ኖረ።


እና​ን​ተስ ከአ​ባ​ታ​ችሁ ከሰ​ይ​ጣን ናችሁ፤ የአ​ባ​ታ​ች​ሁ​ንም ፈቃድ ልታ​ደ​ርጉ ትወ​ዳ​ላ​ችሁ፤ እርሱ ከጥ​ንት ጀምሮ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ በእ​ው​ነ​ትም አይ​ቆ​ምም፤ በእ​ርሱ ዘንድ እው​ነት የለ​ምና፤ ሐሰ​ት​ንም በሚ​ና​ገ​ር​በት ጊዜ ከራሱ አን​ቅቶ ይና​ገ​ራል፤ ሐሰ​ተኛ ነውና፤ የሐ​ሰ​ትም አባት ነውና።


ብላ​ቴ​ኖ​ቹም አደጉ፤ ጐለ​መ​ሱም፤ ዔሳ​ውም አደን የሚ​ያ​ውቅ የበ​ረሃ ሰው ሆነ፤ ያዕ​ቆብ ግን ጭምት ሰው ነበረ፤ በቤ​ትም ይቀ​መጥ ነበር።


የወ​ን​ድ​ሙም ስም ኢዮ​ቤል ነበር፤ እር​ሱም በገ​ና​ንና መሰ​ን​ቆን አስ​ተ​ማረ።


እር​ስ​ዋም “ወንድ ልጅ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ኘሁ” አለች። ደግ​ሞም ወን​ድ​ሙን አቤ​ልን ወለ​ደ​ችው። አቤ​ልም በግ ጠባቂ ሆነ፤ ቃየ​ልም ምድ​ርን የሚ​ያ​ርስ ሆነ።


ላሜ​ሕም ለራሱ ሁለት ሚስ​ቶ​ችን አገባ፤ የአ​ን​ዲቱ ስም ዓዳ፥ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ይቱ ስም ሴላ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች