Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 37:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ወስ​ደ​ውም ወደ ጕድ​ጓድ ጣሉት፤ ጕድ​ጓ​ዱም ውኃ የሌ​ለ​በት ባዶ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ይዘውም ወደ ጕድጓድ ጣሉት፤ ጕድጓዱም ውሃ የሌለበት ደረቅ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ወስደውም ወደ ጉድጓድ ጣሉት፥ ጉድጓዱም ውኃ የሌለበት ደረቅ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ዮሴፍንም ወስደው ውሃ በሌለው ደረቅ ጒድጓድ ውስጥ ጣሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 በብዙ ኅብር ያጌጠቺቱ ቀሚሱን ገፈፋት ወስደውም ወደ ጕድጓድ ጣሉት ጕድጓዱም ውኃ የሌለበት ደረቅ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 37:24
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዮሴፍ ወደ ወን​ድ​ሞቹ በቀ​ረበ ጊዜ የለ​በ​ሳ​ትን በብዙ ኅብር ያጌ​ጠ​ቺ​ውን ቀሚ​ሱን ገፈ​ፉት፤


እን​ጀ​ራም ሊበሉ ተቀ​መጡ፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም በአ​ነሡ ጊዜ እነሆ፥ ይስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያን ነጋ​ድ​ያን ከገ​ለ​ዓድ ሲመጡ አዩ፤ ግመ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም ሽቱና በለ​ሳን፥ ከር​ቤም ተጭ​ነው ነበር። ወደ ግብፅ ሀገ​ርም ሊያ​ራ​ግፉ ይሄዱ ነበር።


እነ​ር​ሱም እርስ በር​ሳ​ቸው እን​ዲህ ተባ​ባሉ፥ “በእ​ው​ነት ወን​ድ​ማ​ች​ንን በድ​ለ​ናል፤ እኛን በመ​ማ​ጠን ነፍሱ ስት​ጨ​ነቅ አይ​ተን አል​ሰ​ማ​ነ​ው​ምና፤ ስለ​ዚህ ይህ መከራ መጣ​ብን።”


አቤቱ፥ ሰው​ንና እን​ስ​ሳን ታድ​ና​ለህ። አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ት​ህን እንደ አበ​ዛህ፥ የሰው ልጆች በክ​ን​ፎ​ችህ ጥላ ይታ​መ​ናሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጠ​ብ​ቀ​ዋል፥ ሕያ​ውም ያደ​ር​ገ​ዋል፥ በም​ድር ላይም ያስ​መ​ሰ​ግ​ነ​ዋል፥ በጠ​ላ​ቶቹ እጅ አሳ​ልፎ አይ​ሰ​ጠ​ውም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በደ​መ​ናት ማን ይተ​ካ​ከ​ለ​ዋል? ከአ​ማ​ል​ክ​ትስ ልጆች እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማን ይመ​ስ​ለ​ዋል?


አቤቱ የኀ​ያ​ላን አም​ላክ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? አቤቱ፥ አንተ ብርቱ ነህ፥ እው​ነ​ትም ይከ​ብ​ብ​ሃል።


ኤር​ም​ያ​ስ​ንም ወሰ​ዱት፤ በግ​ዞት ቤትም አደ​ባ​ባይ ወደ ነበ​ረው ወደ ንጉሡ ልጅ ወደ መል​ክያ ጕድ​ጓድ ውስጥ ጣሉት፤ ኤር​ም​ያ​ስ​ንም በገ​መድ አወ​ረ​ዱት። በጕ​ድ​ጓ​ዱም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውኃ አል​ነ​በ​ረ​በ​ትም፤ ኤር​ም​ያ​ስም ወደ ጭቃው ውስጥ ገባ።


ሬስ። ስለ እርሱ፥ “በአ​ሕ​ዛብ ውስጥ በጥ​ላው በሕ​ይ​ወት እን​ኖ​ራ​ለን” ያል​ነው፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀባ፥ የሕ​ይ​ወ​ታ​ችን እስ​ት​ን​ፋስ፥ በወ​ጥ​መ​ዳ​ቸው ተያዘ።


ለአንቺም ደግሞ ስለ ቃል ኪዳንሽ ደም፥ እስሮችሽን ውኃ ከሌለበት ጕድጓድ አውጥቻለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች