Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 34:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ከእ​ኛም ጋር ተቀ​መጡ፤ ምድ​ራ​ች​ንም በፊ​ታ​ችሁ ሰፊ ናት፤ ኑሩ​ባት፤ ነግ​ዱም፤ ግዙ​አ​ትም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ዐብራችሁንም መኖር ትችላላችሁ፤ አገራችን አገራችሁ ናት፤ ኑሩባት፤ ነግዱባት፤ ሀብት ንብረትም አፍሩባት።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ከእኛም ጋር ተቀመጡ፥ ምድሪቱም እንደፈለጋችሁ ሁኑባት፥ ኑሩባት፥ ነግዱባትም፥ ሀብትም አፍሩባት።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 በዚህ ዐይነት በአገራችን ላይ ከእኛ ጋር መኖር ትችላላችሁ፤ በፈለጋችሁበት ስፍራ በመዘዋወር እየሠራችሁና እየነገዳችሁ ርስትም ይዛችሁ መኖር ትችላላችሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ከእኝም ጋር ተቀመጡ ምድሪቱም በፊታችሁ ናት ኑሩባት ነግዱም ግዙአትም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 34:10
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነሆ፥ ምድር ሁሉ በፊ​ትህ አይ​ደ​ለ​ች​ምን? ከእኔ ትለይ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ አንተ ወደ ግራው ብት​ሄድ እኔ ወደ ቀኝ እሄ​ዳ​ለሁ፤ አን​ተም ወደ ቀኙ ብት​ሄድ እኔ ወደ ግራ እሄ​ዳ​ለሁ።”


አቤ​ሜ​ሌ​ክም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “እነሆ፥ ምድሬ በፊ​ትህ ናት፤ በወ​ደ​ድ​ኸው ተቀ​መጥ።”


ሴኬ​ምም አባ​ቷ​ንና ወን​ድ​ሞ​ች​ዋን እን​ዲህ አለ፥ “በፊ​ታ​ችሁ ሞገ​ስን በአ​ገኝ የም​ት​ሉ​ትን ሁሉ እሰ​ጣ​ለሁ።


ጋብ​ቾ​ችም ሁኑን፤ ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁን ስጡን፤ እና​ን​ተም የእ​ኛን ሴቶች ልጆች ለል​ጆ​ቻ​ችሁ ውሰዱ።


ታና​ሹ​ንም ወን​ድ​ማ​ች​ሁን አም​ጡ​ልኝ፤ ሰላ​ማ​ው​ያን እንጂ ሰላ​ዮች አለ​መ​ሆ​ና​ች​ሁ​ንም በዚህ ዐው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ ወን​ድ​ማ​ች​ሁ​ንም እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም በሀ​ገ​ራ​ችን ትነ​ግ​ዳ​ላ​ችሁ።’ ”


እስ​ራ​ኤ​ልም በግ​ብፅ ምድር በጌ​ሤም ሀገር ተቀ​መጠ፤ እር​ስ​ዋም ርስ​ታ​ቸው ሆነች፤ በዙ፤ እጅ​ግም ተባዙ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች