ዘፍጥረት 32:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፥ “ለጌታዬ ለዔሳው፦ ባሪያህ ያዕቆብ እንዲህ አለ ብላችሁ ንገሩት፦ በላባ ዘንድ በስደት ተቀመጥሁ፤ እስከ ዛሬ ድረስ ቈየሁ፤ ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፤ “ጌታዬን ዔሳውን እንዲህ ትሉታላችሁ፤ ‘አገልጋይህ ያዕቆብ እንዲህ ብሏል በሉት፤ “ከላባ ዘንድ ተቀምጬ እስከ አሁን ድረስ እዚያው ኖርሁ፤ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፦ “ለጌታዬ ለዔሳው፥ አገልጋይህ ያዕቆብ እንዲህ ይላል፥ ‘በላባ ዘንድ በስደት ተቀመጥሁ፥ እስከ አሁን ድረስ ቆየሁ፥’” ብላችሁ ንገሩት ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 እንዲህም በማለት አዘዛቸው፥ “ለጌታዬ ለዔሳው እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፤ ‘ታማኝ አገልጋይህ እኔ ያዕቆብ እስከ አሁን የቈየሁት ከላባ ጋር እንደ ነበር ልነግርህ እወዳለሁ፤ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፦ ለጌታዬ ለዔሳው፦ ባሪያህ ያዕቆብ እንዲህ አለ ብላችሁ ንገሩች፦ በላባ ዘንድ በስደት ተቀመጥሁ እስከ አሁን ድረስ ቆየሁ፤ ምዕራፉን ተመልከት |