Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 31:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ሐው​ል​ቱን ዘይት በቀ​ባ​ህ​ባት፥ በዚ​ያች ለእኔ ስእ​ለት በተ​ሳ​ል​ህ​ባት ሀገር የተ​ገ​ለ​ጥ​ሁ​ልህ ፈጣ​ሪህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ። አሁ​ንም ተነ​ሥ​ተህ ከዚህ ሀገር ውጣ፤ ወደ ተወ​ለ​ድ​ህ​ባ​ትም ምድር ተመ​ለስ፤ እኔም ከአ​ንተ ጋር እኖ​ራ​ለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 የድንጋይ ሐውልት በማቆም ዘይት ቀብተህ የተሳልህባት የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ፤ አሁንም ይህን አገር ፈጥነህ ልቀቅና ወደ ተወለድህበትም ምድር ተመልሰህ ሂድ’ አለኝ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ሐውልት የቀባህበት እና ለእኔ ስእለት የተሳልህበት የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ፥ አሁንም ተነሥተህ ከዚህ ምድር ውጣ፥ ወደ ተወለድህበትም ምድር ተመለስ።’”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 የመታሰቢያ ድንጋይ አቁመህ ዘይት በመቀባት በተሳልክበት ቦታ በቤትኤል የተገለጥኩልህ አምላክህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ አሁንም ከዚህ አገር በፍጥነት ወጥተህ ወደ ተወለድክበት አገር ተመለስ።’ ”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ሐውልት የቀባህበት በዚያም ለእኔ ስእለት የተሳልህበት የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ አሁንም ተነሥተህ ከዚህ አገር ውጣ ወደ ተወለድህበትም ምድር ተመለስ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 31:13
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ልም፦ ‘ያዕ​ቆብ ያዕ​ቆብ’ አለኝ፤ እኔም፦ ‘እነ​ሆኝ ምን​ድን ነው?’ አል​ሁት።


ራሔ​ልና ልያም መል​ሰው እን​ዲህ አሉት፥ “በአ​ባ​ታ​ችን ቤት ለእኛ ድርሻ ወይም ርስት በውኑ አለን?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያዕ​ቆ​ብን፥ “ወደ አባ​ት​ህና ወደ ዘመ​ዶ​ችህ ሀገር ተመ​ለስ፤ እኔም ከአ​ንተ ጋር እሆ​ና​ለሁ” አለው።


ያዕ​ቆ​ብም አለ፥ “የአ​ባቴ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ ሆይ፥ የአ​ባቴ የይ​ስ​ሐቅ አም​ላክ ሆይ፥ ‘ወደ ምድ​ርህ ወደ ተወ​ለ​ድ​ህ​በ​ትም ስፍራ ተመ​ለስ፤ በጎ​ነ​ት​ንም አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለሁ’ ያል​ኸኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያዕ​ቆ​ብን አለው፥ “ተነ​ሥ​ተህ ወደ ቤቴል ውጣ፤ በዚ​ያም ኑር፤ ከወ​ን​ድ​ምህ ከዔ​ሳው ፊት በሸ​ሸህ ጊዜ ለተ​ገ​ለ​ጥ​ሁ​ልህ ለእኔ መሥ​ው​ያን ሥራ።”


በዚ​ያም መሠ​ው​ያ​ዉን ሠራ፤ የዚ​ያ​ንም ቦታ ስም ቤቴል ብሎ ጠራው፤ እርሱ ከወ​ን​ድሙ ከዔ​ሳው ፊት በሸ​ሸ​በት ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ ተገ​ል​ጦ​ለት ነበ​ርና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች