Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 30:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ልያም፥ “ባሌን መው​ሰ​ድሽ አይ​በ​ቃ​ሽ​ምን? አሁን ደግሞ የል​ጄን እን​ኮይ ልት​ወ​ስጂ ትፈ​ል​ጊ​ያ​ለ​ሽን?” አለ​ቻት። ራሔ​ልም “እን​ኪ​ያስ ስለ ልጅሽ እን​ኮይ በዚ​ህች ሌሊት ከአ​ንቺ ጋር ይደር” አለች፤ ሰጠ​ቻ​ትም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ልያም፣ “ባሌን የቀማሽኝ አነሰና የልጄን እንኮይ ደግሞ ልትወስጂ አማረሽ?” አለቻት። ራሔልም፣ “ስለ ልጅሽ እንኮይ ዛሬ ከአንቺ ጋራ ይደር” አለቻት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 “የልጅሽን እንኮይ ስጪኝ” አለቻት። እርሷም፦ “ባሌን መውሰድሽ በውኑ ጥቂት ነገር ነውን? አሁን ደግሞ የልጄን እንኮይ ልትወስጂ ትፈልጊያለሽን?” አለቻት። ራሔልም፦ “እንኪያስ ስለ ልጅሽ እንኮይ በዚህች ሌሊት ከአንቺ ጋር ይተኛ” አለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ልያም “ባሌን የነጠቅሽኝ አንሶሽ፥ አሁን ደግሞ ልጄ ያመጣልኝን እንኮይ መቀማት ትፈልጊያለሽን?” አለቻት። ራሔልም “ከልጅሽ እንኮይ ስጪኝና ዛሬ ሌሊት ያዕቆብ ካንቺ ጋር ይደር” አለቻት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ራሔልም ልያን፦ የልጅሽን እንኮይ ስጪኝ አለቻት። እርስዋም፦ ባሌን መውሰድሽ በውኑ ጥቂት ነገር ነውን? አሁን ደግሞ የልጄን እንኮይ ልትወስጂ ትፈልጊአለሽን? አለቻት። ራሔልም፦ እንኪያስ ስለ ልጅሽ እንኮይ በዚህች ሌሊት ከአንቺ ጋር ይተኛ አለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 30:15
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሮቤል ስንዴ በሚ​ታ​ጨ​ድ​በት ወራት ወጣ፤ በእ​ር​ሻም እን​ኮይ አገኘ፥ ለእ​ናቱ ለል​ያም አመ​ጣ​ላት። ራሔ​ልም ልያን፥ “የል​ጅ​ሽን እን​ኮይ ስጪኝ” አለ​ቻት።


ያዕ​ቆ​ብም ሲመሽ ከዱር ገባ፤ ልያም ልት​ቀ​በ​ለው ወጣች፤ እን​ዲ​ህም አለ​ችው፥ “እኔ ዘንድ ታድ​ራ​ለህ፤ በልጄ እን​ኮይ በእ​ር​ግጥ ተስ​ማ​ም​ቼ​ሃ​ለ​ሁና።”


እር​ሱም አለ፥ “እና​ንተ የዳ​ዊት ቤት ሆይ፥ ስሙ፤ በውኑ ሰውን ማድ​ከ​ማ​ችሁ ቀላል ነውን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታደ​ክ​ማ​ላ​ችሁ፤


አንቺ ግን በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው አል​ሄ​ድ​ሽም፤ እንደ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም አላ​ደ​ረ​ግ​ሽም፤ ያው ለአ​ንቺ ጥቂት ነበ​ረና በመ​ን​ገ​ድሽ ሁሉ ከእ​ነ​ርሱ የሚ​ከፋ ኀጢ​አት አደ​ረ​ግሽ።


በም​ድረ በዳ ትገ​ድ​ለን ዘንድ፥ በእ​ኛም ላይ አለ​ቃ​ችን ትሆን ዘንድ ወተ​ትና ማር ከም​ታ​ፈ​ስ​ሰው ምድር ያወ​ጣ​ኸን አነ​ሰ​ህን?


ለእ​ኔስ በእ​ና​ንተ ዘንድ መመ​ስ​ገን ውር​ደት ነው፤ ጻድቅ ብት​ሉኝ፥ በመ​ዋቲ ሰው ዘን​ድም ቸር ብላ​ችሁ ብታ​ከ​ብ​ሩኝ እኔ ለራሴ አል​ፈ​ር​ድም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች