Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 3:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እባ​ብም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ከፈ​ጠ​ራ​ቸው ከም​ድር አራ​ዊት ሁሉ ይልቅ ተን​ኰ​ለኛ ነበር። እባ​ብም ሴቲ​ቱን “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በገ​ነት ካለው ዛፍ ሁሉ አት​ብሉ ያላ​ችሁ ለም​ን​ድን ነው?” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እባብ እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠራቸው የዱር አራዊት ሁሉ ተንኰለኛ ነበረ፤ ሴቲቱንም፣ “በርግጥ እግዚአብሔር፣ ‘በአትክልቱ ስፍራ ካሉ ዛፎች ከማናቸውም እንዳትበሉ’ ብሏልን?” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ጌታ እግዚአብሔርም ከፈጠረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ እባብ ተንኰለኛ ነበረ። ሴቲቱንም፦ “በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ አንዳች እንዳትበሉ አዝዞአልን?” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠራቸው አራዊት ሁሉ፥ እባብ እጅግ ተንኰለኛ ነበረ፤ ስለዚህ እባብ “በአትክልቱ ቦታ ካሉት ዛፎች ሁሉ ፍሬ እንዳትበሉ በእርግጥ እግዚአብሔር አዞአችኋልን?” ሲል ሴቲቱን ጠየቃት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እባብም እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ ተንኵለኚ ነበረ። ሴቲቱንም፤ በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአል? አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 3:1
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንዱ ቢወ​ድቅ ሁለ​ተ​ኛው ያነ​ሣ​ዋ​ልና፥ አንድ ብቻ​ውን ሆኖ በወ​ደቀ ጊዜ ግን የሚ​ያ​ነ​ሣው ሁለ​ተኛ የለ​ው​ምና ወዮ​ለት።


በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ጣኑ እባብ ደራ​ጎን ላይ፥ በክ​ፉ​ውም እባብ ደራ​ጎን ላይ ልዩ፥ ታላ​ቅና ብርቱ ሰይ​ፍን ያመ​ጣል። በባ​ሕ​ርም ውስጥ ያለ​ውን ዘንዶ ይገ​ድ​ለ​ዋል።


“እነሆ እኔ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።


ፈታኝም ቀርቦ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል!” አለው።


“ ‘መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል፤ እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል’ ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ወደ ታች ራስህን ወርውር” አለው።


“ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ” አለው።


ይህም አያ​ስ​ደ​ን​ቅም፤ ሰይ​ጣን ራሱ ተለ​ውጦ እንደ ብር​ሃን መል​አክ ይመ​ስ​ላ​ልና።


ነገር ግን እባብ ሔዋ​ንን በተ​ን​ኰሉ እን​ዳ​ሳ​ታት፥ አሳ​ባ​ችሁ ከክ​ር​ስ​ቶስ የዋ​ህ​ነ​ትና ንጽ​ሕና ምና​ል​ባት እን​ዳ​ይ​ለ​ወጥ ብዬ እፈ​ራ​ለሁ።


እንዲሁም እናንተ ባሎች ሆይ! ደካማ ፍጥረት ስለ ሆኑ ከሚስቶቻችሁ ጋር በማስተዋል አብራችሁ ኑሩ፤ ጸሎታችሁ እንዳይከለከል አብረው ደግሞ የሕይወትን ጸጋ እንደሚወርሱ አድርጋችሁ አክብሩአቸው።


እባቡም ሴቲቱ በወንዝ እንድትወሰድ ሊያደርግ ወንዝ የሚያህልን ውሃ ከአፉ በስተ ኋላዋ አፈሰሰ።


ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።


የቀደመውንም እባብ ዘንዶውን እርሱም ዲያብሎስና ሰይጣን የተባለውን ያዘው፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች