Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 27:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 ይስ​ሐ​ቅም መለሰ ዔሳ​ው​ንም አለው፥ “እነሆ ጌታህ አደ​ረ​ግ​ሁት፤ ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንም ሁሉ ለእ​ርሱ ተገ​ዦች አደ​ረ​ግ​ኋ​ቸው፤ እህ​ሉን፥ ወይ​ኑ​ንና ዘይ​ቱ​ንም አበ​ዛ​ሁ​ለት፤ ለአ​ንተ ግን፥ ልጄ ሆይ፥ ምን ላድ​ር​ግ​ልህ?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 ይሥሐቅም ለዔሳው፣ “በአንተ ላይ የበላይነት እንዲኖረው፣ ወንድሞቹ ሁሉ አገልጋዮቹ እንዲሆኑ፣ እህሉ፣ የወይን ጠጁም የተትረፈረፈ እንዲሆንለት መርቄዋለሁ። ታዲያ ልጄ፣ ለአንተ ምን ላደርግልህ እችላለሁ?” ሲል መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 ይስሐቅም መለሰ ዔሳውንም አለው፦ “እነሆ፥ ጌታህ አደረግሁት፥ ወንድሞቹንም ሁሉ ለእርሱ ተገዦች ይሆኑ ዘንድ ሰጠሁት፥ በእህልም በወይንም አበረታሁት፥ ለአንተ ግን፥ ልጄ ሆይ፥ ምን ላድርግ?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 ይስሐቅም “ቀደም ብዬ እርሱን የአንተ ጌታ አድርጌዋለሁ፤ ወንድሞቹ ሁሉ የእርሱ አገልጋዮች እንዲሆኑ አድርጌአለሁ፤ እህልና የወይን ጠጅ እንዲበዛለት አድርጌአለሁ፤ ልጄ ሆይ! እንግዲህ ለአንተ ምን ላደርግልህ እችላለሁ?” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 ይስሐቅም መለሰ ዔሳውንም አለው፦ እነሆ ጌታህ አደረግሁት ወንድሞቹንም ሁሉ ለእርሱ ተገዦች ይሆኑ ዘንድ ሰጠሁት በእህልም በወይንም አበረታሁት ለአንተ ግን ልጄ ሆይ ምን ላድርግ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 27:37
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አላት፥ “ሁለት ሕዝ​ቦች በማ​ኅ​ፀ​ንሽ አሉ፤ ሁለ​ቱም ሕዝብ ከሆ​ድሽ ይወ​ለ​ዳሉ፤ ሕዝ​ብም ከሕ​ዝብ ይበ​ረ​ታል፤ ታላ​ቁም ለታ​ናሹ ይገ​ዛል።”


መላ​ዋን ኤዶ​ም​ያ​ስን ይጠ​ብቁ ዘንድ በኤ​ዶ​ም​ያስ ሁሉ ጭፍ​ሮ​ችን አኖረ፤ ኤዶ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ ለን​ጉሥ ዳዊት ገባ​ሮች ሆኑ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዳዊ​ትን በሚ​ሄ​ድ​በት ቦታ ሁሉ ጠበ​ቀው።


ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ወደ ኦፌር ሄደው ወርቅ ያመጡ ዘንድ በተ​ር​ሴስ መር​ከ​ብን ሠራ፤ ነገር ግን መር​ከ​ቢቱ በጋ​ሴ​ዎ​ን​ጋ​ቤር ተሰ​ብ​ራ​ለ​ችና አል​ሄ​ደ​ችም።


እስ​ራ​ኤ​ልም ተማ​ምኖ፥ በያ​ዕ​ቆብ ምድር ብቻ​ውን፥ በስ​ን​ዴና በወ​ይን ምድር ይኖ​ራል፤ ሰማይ ከደ​መ​ናና ከጠል ጋር ለአ​ንተ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች