Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 27:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 ይስ​ሐ​ቅም ዔሳ​ውን አለው፥ “ወን​ድ​ምህ በተ​ን​ኰል መጥቶ በረ​ከ​ት​ህን ወሰ​ደ​ብህ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ይሥሐቅም፣ “ወንድምህ መጥቶ አታልሎኝ ምርቃትህን ወስዶብሃል” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 እርሱም፦ “ወንድምህ በተንኮል ገብቶ በረከትህን ወሰደብህ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 ይስሐቅም “ወንድምህ መጥቶ እኔን በማታለል የአንተን ምርቃት ወስዶብሃል” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 እርሱም፦ ወንድምህ በተንኮል ገብቶ በረከትህን ወሰደብህ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 27:35
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይስ​ሐ​ቅም እጅግ ደነ​ገጠ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ያደ​ነ​ውን አደን ወደ እኔ ያመ​ጣው ማን ነው? አንተ ሳት​መ​ጣም ከሁሉ በላሁ፤ ባረ​ክ​ሁ​ትም፤ እር​ሱም የተ​ባ​ረከ ነው።”


በነ​ጋም ጊዜ እነሆ ልያ ነበ​ረች፤ ያዕ​ቆ​ብም ላባን፥ “ምነው እን​ደ​ዚህ አደ​ረ​ግ​ህ​ብኝ? ያገ​ለ​ገ​ል​ሁህ ስለ ራሔል አል​ነ​በ​ረ​ምን? ለምን አታ​ለ​ል​ኸኝ?” አለው።


አሁ​ንም የበ​ዓ​ልን ነቢ​ያት ሁሉ፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም ሁሉ፥ ካህ​ና​ቱ​ንም ሁሉ ወደ እኔ ጥሩ፤ ማንም እን​ዳ​ይ​ቀር፤ ለበ​ዓል ታላቅ መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ር​ባ​ለሁ፤ የቀ​ረ​ውም ሁሉ በሕ​ይ​ወት አይ​ኖ​ርም” አላ​ቸው። ኢዩ ግን የበ​ዓ​ልን አገ​ል​ጋ​ዮች ያጠፋ ዘንድ በተ​ን​ኮል ይህን አደ​ረገ።


በውኑ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት የም​ት​ና​ገሩ አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምን? በፊቱ ሽን​ገ​ላን ታወ​ራ​ላ​ች​ሁን?


ወን​ድ​ምም ሁሉ ያሰ​ና​ክ​ላ​ልና፥ ባል​ን​ጀ​ራም ሁሉ በጠ​ማ​ማ​ነት ይሄ​ዳ​ልና እና​ንተ ሁሉ ከባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ችሁ ተጠ​ን​ቀቁ፤ በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁም አት​ታ​መኑ።


ለሁላችን አንድ አባት ያለን አይደለምን? አንድ አምላክስ የፈጠረን አይደለምን? የአባቶቻችንን ቃል ኪዳን ለማስነቀፍ እኛ እያንዳዳችን ወንድማችንን ስለ ምን አታለልን?


ነገር ግን ከእኛ ያይ​ደለ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ገኘ ታላቅ ኀይል ይሆን ዘንድ በሸ​ክላ ዕቃ ውስጥ ይህ መዝ​ገብ አለን።


አስቀድመን ደግሞ እንዳልናችሁና እንደ መሰከርንላችሁ፥ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነውና፥ ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ፤ ወንድሙንም አያታልል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች