Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 24:54 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

54 ከዚ​ህም ሁሉ በኋላ እርሱ፥ ከእ​ርሱ ጋር ያሉ​ትም በሉ፤ ጠጡም፤ በዚ​ያም አደሩ፤ በማ​ለ​ዳም ተነ​ሥቶ፥ “ወደ ጌታዬ እሄድ ዘንድ አሰ​ና​ብ​ቱኝ” አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

54 እርሱና ዐብረውት የነበሩ ሰዎችም በልተው፣ ጠጥተው እዚያው ዐደሩ። በማግስቱም ጧት ሲነሡ፣ የአብርሃም አገልጋይ፣ “እንግዲህ ወደ ጌታዬ እንድመለስ አሰናብቱኝ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

54 እርሱም ከእርሱም ጋር ያሉት በሉ ጠጡም፥ ከዚያም አደሩ፥ ማልደውም ተነሡና፦ “ወደ ጌታዬ እሄድ ዘንድ አሰናብቱኝ” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

54 ከዚህ በኋላ የአብርሃም አገልጋይና አብረውት የነበሩ ሰዎች በልተው ጠጥተው እዚያው ዐደሩ፤ ጠዋት በተነሡ ጊዜ የአብርሃም አገልጋይ “እንግዲህ ወደ ጌታዬ እንድመለስ ፍቀዱልኝ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

54 እርሱም ከእርሱም ጋር ያሉት በሉ ጠጡም ከዚያም አደሩ ማልደውም ተነሡና፦ ወደ ጌታዬ እሄድ ዘንድ አሰናብቱኝ አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 24:54
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ገ​ዴን አቅ​ን​ቶ​ልኝ ሳለ አታ​ዘ​ግ​ዩኝ፤ ወደ ጌታዬ እሄድ ዘንድ አሰ​ና​ብ​ቱኝ” አላ​ቸው።


እኅ​ታ​ቸ​ው​ንም ርብ​ቃን ሞግ​ዚ​ቷ​ንም ከገ​ን​ዘብ ጋር፥ የአ​ብ​ር​ሃ​ምን ሎሌና ሰዎ​ቹ​ንም አሰ​ና​በ​ቱ​አ​ቸው።


ከዚህ ዘመን ይልቅ ያለ​ፈው ዘመን ለምን ተሻለ? ብለህ አት​ና​ገር፤ የዚ​ህን ነገር በጥ​በብ አት​ጠ​ይ​ቅ​ምና።


ነገርን የሚረዳ፥ በሥራውም ብልህ የሆነ ሰው፥ ወደ ነገሥታት ይቀርባል፤ በተዋረዱ ሰዎችም ፊት አይቆምም።


የሳ​ዶቅ ልጅ አኪ​ማ​ሖስ ግን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጠ​ላ​ቶቹ እጅ እንደ ፈረ​ደ​ለት ፈጥኜ ሄጄ ለን​ጉሥ የም​ሥ​ራች ልን​ገ​ርን?” አለ።


ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን አሰ​ና​በ​ታ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “በመ​ን​ገድ እርስ በር​ሳ​ችሁ አት​ጣሉ።”


ራሔ​ልም ዮሴ​ፍን ከወ​ለ​ደች በኋላ ያዕ​ቆብ ላባን እን​ዲህ አለው፥ “ወደ ስፍ​ራዬ፥ ወደ ሀገ​ሬም እመ​ለስ ዘንድ አሰ​ና​ብ​ተኝ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች