Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 24:48 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

48 ይህ​ንም ነገር ከአ​ን​ደ​በቷ በሰ​ማሁ ጊዜ እጅግ ደስ አሰ​ኘ​ችኝ። ለጆ​ሮ​ዎ​ች​ዋም ጉት​ቻ​ዎ​ችን ለእ​ጆ​ች​ዋም አም​ባ​ሮ​ችን አድ​ርጌ አስ​ጌ​ጥ​ኋት። ደስ ባሰ​ኘ​ች​ኝም ጊዜ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገ​ድሁ፤ የጌ​ታ​ዬን የወ​ን​ድ​ሙን ልጅ ለልጁ እወ​ስድ ዘንድ በቀና መን​ገድ የመ​ራ​ኝን የጌ​ታ​ዬን የአ​ብ​ር​ሃ​ምን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገ​ንሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

48 ተደፍቼም ለእግዚአብሔር ሰገድሁ፤ ለጌታዬ ወንድም የልጅ ልጅ የሆነችውን ቈንጆ፣ ለጌታዬ ልጅ እንዳገኝለት በቀና መንገድ የመራኝን የጌታዬ የአብርሃምን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገንሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

48 በግምባሬም አጎነበስሁ፥ ለእግዚአብሔርም ሰገድሁ፥ የጌታዬን የወንድሙን ልጅ ለልጁ እወስድ ዘንድ በቀና መንገድ የመራኝን የጌታዬን የአብርሃምን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገንሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

48 ከዚህ በኋላ ለጌታዬ ልጅ ሚስት የምትሆነዋን ሴት ወዳገኘሁበት ወደ ጌታዬ ወንድም ቤት በቀና መንገድ ለመራኝ ለእግዚአብሔር በጒልበቴ ተንበርክኬ ሰገድሁ፤ የጌታዬን የአብርሃምን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገንኩ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

48 በግምባሬም አጎነበስሁ፥ ለእግዚአብሔርም ሰገድሁ፤ የጌታዬን የወንድሙን ልጅ ለልጁ እወስድ ዘንድ በቀና መንገድ የመራኝን የጌታዬን የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገንሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 24:48
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ባቱ​ኤ​ልም ርብ​ቃን ወለደ፤ ሚልካ ለአ​ብ​ር​ሃም ወን​ድም ለና​ኮር የወ​ለ​ደ​ች​ለት ስም​ንቱ ልጆች እነ​ዚህ ናቸው።


የአ​ብ​ር​ሃ​ምም ሎሌ ነገ​ራ​ቸ​ውን በሰማ ጊዜ ወደ ምድር ወድቆ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገደ።


በአ​ም​ላ​ካ​ችን ፊት ራሳ​ች​ንን እና​ዋ​ርድ ዘንድ፥ ከእ​ር​ሱም የቀ​ና​ውን መን​ገድ ለእ​ኛና ለል​ጆ​ቻ​ችን፥ ለን​ብ​ረ​ታ​ች​ንም ሁሉ እን​ለ​ምን ዘንድ በዚያ በአ​ኅዋ ወንዝ አጠ​ገብ ጾምን አወ​ጅሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ቅ​ደሱ ተና​ገረ፥ ደስ ይለ​ኛል፥ ሰቂ​ማ​ንም እካ​ፈ​ላ​ለሁ፥ የሸ​ለቆ ቦታ​ዎ​ችን እሰ​ፍ​ራ​ለሁ።


ምድር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትፈ​ራ​ዋ​ለች፥ በዓ​ለም የሚ​ኖሩ ሁሉም ከእ​ርሱ የተ​ነሣ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።


እንደ በጎች ሞት በሲ​ኦል ይጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋል፥ ቅኖ​ችም በማ​ለዳ ይገ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፥ ረድ​ኤ​ታ​ቸ​ውም ከክ​ብ​ራ​ቸው ተለ​ይታ በሲ​ኦል ትጠ​ፋ​ለች።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሥር​ዐ​ቱ​ንና ሕጉን መስ​ክ​ር​ላ​ቸው፤ የሚ​ሄ​ዱ​በ​ት​ንም መን​ገድ፥ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ት​ንም ሥራ ሁሉ አሳ​ያ​ቸው።


የጥበብን መንገዶች አስተምርሃለሁና፤ በቀናች ጎዳና መራሁህ።


ታዳ​ጊህ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ፥ እን​ዲህ ይላል፥ “እኔ የሚ​ረ​ባ​ህን ነገር የማ​ስ​ተ​ም​ርህ የም​ት​ሄ​ድ​ባ​ት​ንም መን​ገድ እን​ዴት እን​ደ​ም​ታ​ገኝ የም​መ​ራህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች