ዘፍጥረት 20:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 አቤሜሌክም በጥዋት ተነሣ፤ ብላቴኖቹንም ሁሉ ጠራ፤ ይህንም ነገር ሁሉ በጆሮአቸው ተናገረ፤ ቤተ ሰዎቹም ሁሉ እግዚአብሔርን እጅግ ፈሩ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 በማግስቱም ማለዳ፣ አቢሜሌክ ሹማምቱን ሁሉ ጠርቶ፣ የሆነውን ሁሉ ነገራቸው፤ እነርሱም ታላቅ ፍርሀት ዐደረባቸው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 አቢሜሌክም በነገታው ማልዶ ተነሣ፥ ባለሟሎቹንም ሁሉ ጠርቶ የሆነውን ነገር ሁሉ ነገራቸው፥ ሰዎቹም እጅግ ደነገጡ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 በማግስቱ ጠዋት በማለዳ አቤሜሌክ ባለሟሎቹን ጠርቶ የሆነውን ነገር ሁሉ በተረከላቸው ጊዜ ደነገጡ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 አቢሜሌክም በነገታው ማለደ፥ ባሪያዎቹንም ሁሉ ጠራ ይህንንም ነገር ሁሉ በጆሮአቸው ተናገረ ስዎቹም እጅግ ፈሩ። ምዕራፉን ተመልከት |