Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 19:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ጎህም በቀ​ደደ ጊዜ መላ​እ​ክት ሎጥን፥ “ተነሣ፤ ሚስ​ት​ህ​ንና ከዚህ ያሉ​ትን ሁለ​ቱን ሴቶች ልጆ​ች​ህን ውሰድ፤ አን​ተም በከ​ተ​ማ​ዪቱ ሰዎች ኀጢ​አት እን​ዳ​ት​ጠፋ” እያሉ ያስ​ቸ​ኩ​ሉት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ሲነጋጋም መላእክቱ ሎጥን፣ “ከከተማዪቱ ጋራ ዐብራችሁ እንዳትጠፉ፣ ሚስትህንና ሁለቱን ሴት ልጆችህን ይዘህ ከዚህ ቦታ በፍጥነት ውጣ” ብለው አቻኰሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ጎህም በቀደደ ጊዜ መላእክት ሎጥን፦ “ተነሣ፥ ሚስትህንና ከዚህ ያሉትን ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ውሰድ፥ በከተማይቱ ኃጢአት እንዳትጠፋ” እያሉ ያስቸኩሉት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 በማግስቱ ጠዋት በማለዳ መላእክቱ ሎጥን “ፍጠን! ከተማይቱ ስትጠፋ አብራችሁ እንዳትጠፉ ሚስትህንና ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ይዘህ ከዚህ ውጣ” እያሉ አጣደፉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ጎህም በቀደደ ጊዜ መላእክት ሎጥን፥ ተነሣ ሚስትህንና ከዚህ ያሉትን ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ውስድ በከተማይቱ ኃጢአት እንዳትጠፉ እያሉ ያስቸኵሉት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 19:15
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሎጥም ወጣ፤ ልጆ​ቹን ለሚ​ያ​ገ​ቡት ለአ​ማ​ቾ​ቹም አላ​ቸው፥ “ተነሡ፤ ከዚች ስፍራ ውጡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ​ችን ከተማ ያጠ​ፋ​ታ​ልና።” ለአ​ማ​ቾቹ ግን የሚ​ያ​ፌ​ዝ​ባ​ቸው መሰ​ላ​ቸው።


እር​ሱም በዘ​ገየ ጊዜ እነ​ዚያ መላ​እ​ክት የእ​ር​ሱን እጅ፥ የሚ​ስ​ቱ​ንም እጅ፥ የሁ​ለ​ቱን ሴቶች ልጆ​ቹ​ንም እጅ ይዘው አወ​ጡ​አ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራር​ቶ​ላ​ቸ​ዋ​ልና።


ወደ ሜዳም በወጡ ጊዜ እን​ዲህ አሉት፥ “ራስ​ህን አድን፤ ወደ ኋላም አት​መ​ል​ከት፤ አን​ተ​ንም መከራ እን​ዳ​ታ​ገ​ኝህ በዚች ሀገር በዳ​ር​ቻ​ዋና በተ​ራ​ራዋ አት​ቁም።”


እን​ግ​ዲህ ፍጠ​ንና በዚያ ራስ​ህን አድን፤ ወደ​ዚያ እስ​ክ​ት​ደ​ርስ ድረስ ምንም አደ​ርግ ዘንድ አል​ች​ል​ምና።” ስለ​ዚ​ህም የዚ​ያች ከተማ ስም ሴጎር ተባለ።


እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “በተ​መ​ረ​ጠ​ችው ቀን ሰማ​ሁህ፤ በመ​ዳ​ንም ቀን ረዳ​ሁህ” እነሆ፥ የተ​መ​ረ​ጠ​ችው ቀን ዛሬ ናት።


ከሰማይም ሌላ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ “ሕዝቤ ሆይ! በኀጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች