Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 18:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 አብ​ር​ሃ​ምም ወደ ላሞቹ ሮጠ፤ እጅግ የሰ​ባም ታናሽ ጥጃ ያዘና ለብ​ላ​ቴ​ናው ሰጠው፤ ያዘ​ጋ​ጅም ዘንድ ተቻ​ኮለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ከዚያም ወደ መንጋው በጥድፊያ ሄዶ፣ አንድ ፍርጥም ያለ ሥጋው ገር የሆነ ጥጃ መርጦ ለአገልጋዩ ሰጠው፤ አገልጋዩም ጥጃውን ዐርዶ አዘጋጀው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 አብርሃምም ወደ ላሞቹ ሮጠ፥ እጅግ የሰባም ታናሽ ጥጃ ያዘና ለብላቴናው ሰጠው፥ ያዘጋጅም ዘንድ ተቻኰለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ከዚህ በኋላ አብርሃም ወደ መንጋው ሄደና ለግላጋውንና መልካሙን ጥጃ መርጦ ለአገልጋዩ ሰጠው፤ አገልጋዩም በፍጥነት ዐርዶ አወራርዶ አዘጋጀው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 አብርሃምም ወደ ላሞቹ ሮጠ እጅግ የሰባም ታናሽ ጥጃ ያዘና ለብላቴንው ስጠው፥ ያዘጋጅም ዘንድ ተቻኮለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 18:7
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከአ​መ​ን​ዝ​ሮች ጋር ገን​ዘ​ብ​ህን ሁሉ የጨ​ረሰ ይህ ልጅህ በተ​መ​ለሰ ጊዜ ግን የሰ​ባ​ውን ፍሪዳ አረ​ድ​ህ​ለት።’


እር​ሱም፦ ‘ወን​ድ​ምህ ከሄ​ደ​በት መጣ፤ አባ​ት​ህም የሰ​ባ​ውን ፍሪዳ አረደ፤ በሕ​ይ​ወት አግ​ኝ​ቶ​ታ​ልና’ አለው።


የሰ​ባ​ውን ፍሪ​ዳም አም​ጡና እረዱ፤ እን​ብላ፤ ደስም ይበ​ለን።


ደግሞ ሌሎችን ባሮች ልኮ ‘የታደሙትን እነሆ፥ ድግሴን አዘጋጀሁ፤ ኮርማዎቼና የሰቡት ከብቶቼ ታርደዋል፤ ሁሉም ተዘጋጅቶአል፤ ወደ ሰርጉ ኑ፤ በሉአቸው፤’ አለ።


እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ስሜም በአሕዛብ ዘንድ የተፈራ ነውና በመንጋው ውስጥ ተባት እያለው ለጌታ ተስሎ ነውረኛውን የሚሠዋ ሸንጋይ ሰው ርጉም ይሁን።


ከዝ​ሆን ጥርስ በተ​ሠራ አልጋ ላይ ለሚ​ተኙ፥ በም​ን​ጣ​ፋ​ቸው ደስ ለሚ​ሰኙ፥ ከበ​ጎ​ችም መንጋ ጠቦ​ትን፥ ከጋ​ጥም ውስጥ ጥጃን ለሚ​መ​ገቡ፥


እር​ሱም ግድ አላ​ቸው፤ ወደ እር​ሱም አቀኑ፤ ወደ ቤቱም ገቡ፤ ቂጣ​ንም አስ​ጋ​ገ​ረ​ላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም በሉ።


አብ​ር​ሃ​ምም ወደ ድን​ኳን ወደ ሚስቱ ወደ ሣራ ፈጥኖ ገባና፥ “ሦስት መስ​ፈ​ሪያ የተ​ሰ​ለቀ ዱቄት ፈጥ​ነሽ ለውሺ፤ እን​ጎ​ቻም አድ​ርጊ” አላት።


እር​ጎና መዓር፥ ያን ያዘ​ጋ​ጀ​ው​ንም ጥጃ አመጣ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም አቀ​ረ​በው፤ እር​ሱም ከዛፉ በታች በፊ​ታ​ቸው ቆሞ ያሳ​ል​ፍ​ላ​ቸው ነበር፤ እነ​ር​ሱም በሉ።


ለሴ​ቲ​ቱም የሰባ ጥጃ በቤት ነበ​ራት፤ ፈጥና አረ​ደ​ችው፤ ዱቄ​ቱ​ንም ወስዳ ለወ​ሰ​ችው፤ ቂጣም እን​ጀራ አድ​ርጋ ጋገ​ረ​ችው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች