Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 17:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን የሥ​ጋ​ውን ቍል​ፈት ያል​ተ​ገ​ረዘ፥ ያች ነፍስ ከወ​ገ​ንዋ ተለ​ይታ ትጥፋ፤ ቃል ኪዳ​ኔን አፍ​ር​ሳ​ለ​ችና።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 የሥጋ ሸለፈቱን ያልተገረዘ ማንኛውም ወንድ ኪዳኔን በማፍረሱ ከወገኖቹ ይወገድ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የቍልፈቱን ሥጋ ያልተገረዘ ቈላፍ ሰው ሁሉ፥ ያች ነፍስ ከወገንዋ ተለይታ ትጥፋ፥ ቃል ኪዳኔን አፍርሳለችና።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በሥጋው ያልተገረዘ ወንድ ሁሉ ቃል ኪዳኔን ስላላከበረ ከሕዝቡ ይወገዳል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ቃል ኪዳኔም በሥጋችሁ የዘላለም ቃል ኪዳን ይሆናል። የቍልፈቱን ሥጋ ያልተገረዘ ቆላፍ ሰው ሁሉ ያች ነፍስ ከወገንዋ ተለይታ ትጥፋ ቃል ኪዳኔን አፍርሳለችና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 17:14
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰባት ቀን በቤ​ታ​ችሁ እርሾ አይ​ገኝ፤ እርሾ ያለ​በ​ት​ንም እን​ጀራ የሚ​በላ ሁሉ ያ ሰው ከመ​ጻ​ተ​ኛው ጀምሮ እስከ ሀገር ልጁ ድረስ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ማኅ​በር ተለ​ይቶ ይጥፋ።


ሳይ​ገ​ባው፥ የጌ​ታ​ችን ሥጋም እንደ ሆነ ሳያ​ውቅ፥ ሰው​ነ​ቱ​ንም ሳያ​ነጻ፥ የሚ​በ​ላና የሚ​ጠጣ ለራሱ ፍር​ዱ​ንና መቅ​ሠ​ፍ​ቱን ይበ​ላል፤ ይጠ​ጣ​ልም።


አሁ​ንም ሳይ​ገ​ባው ይህን ኅብ​ስት የበላ፥ ይህ​ንም ጽዋ የጠጣ የጌ​ታ​ችን ሥጋ​ውና ደሙ ስለ​ሆነ ዕዳ አለ​በት።


ከግ​ብፅ ሀገር አወ​ጣ​ቸው ዘንድ እጃ​ቸ​ውን በያ​ዝ​ሁ​በት ቀን ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር እንደ ገባ​ሁት ያለ ቃል ኪዳን አይ​ደ​ለም፤ እነ​ርሱ በኪ​ዳኔ አል​ጸ​ኑ​ምና፥ እኔም ቸል አል​ኋ​ቸው፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ቃሌን ይሰሙ ዘንድ እንቢ ወደ አሉ ወደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው ኀጢ​አት ተመ​ለሱ፥ ያመ​ል​ኩ​አ​ቸ​ውም ዘንድ እን​ግ​ዶ​ችን አማ​ል​ክት ተከ​ተሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤትና የይ​ሁዳ ቤት ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ቃል ኪዳን አፈ​ረሱ።


መን​ገ​ዶች ባድማ ሆኑ፤ የአ​ሕ​ዛ​ብም መፈ​ራት ቀረ፤ ቃል ኪዳ​ና​ቸ​ውም ፈረሰ፤ እንደ ሰውም አል​ተ​መ​ለ​ከ​ታ​ቸ​ውም።


ምድ​ርም በሚ​ቀ​መ​ጡ​ባት ሰዎች ምክ​ን​ያት በደ​ለች፤ ሕጉን ተላ​ል​ፈ​ዋ​ልና፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ለው​ጠ​ዋ​ልና፥ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙ​ንም ቃል ኪዳን አፍ​ር​ሰ​ዋ​ልና።


የበ​ላ​ውም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ነገር አር​ክ​ሶ​አ​ልና ኀጢ​አ​ቱን ይሸ​ከ​ማል፤ ያም ሰው ከሕ​ዝቡ ተለ​ይቶ ይጥፋ።


ከዚህ ርኵ​ሰት ሁሉ ማና​ቸ​ውን የሚ​ያ​ደ​ርግ ያ ሰው ከሕ​ዝቡ መካ​ከል ተለ​ይቶ ይጠ​ፋ​ልና።


ደም የም​ት​በላ ሰው​ነት ሁሉ ያች ሰው​ነት ከሕ​ዝ​ብዋ ተለ​ይታ ትጥፋ።”


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ሳት ከሚ​ቀ​ር​በው ከእ​ን​ስሳ ስብ የሚ​በላ ሁሉ ያች የበ​ላች ሰው​ነት ከሕ​ዝ​ብዋ ተለ​ይታ ትጥፋ።


ሊያ​ሸ​ት​ተ​ውም እንደ እርሱ የሚ​ያ​ደ​ርግ ሰው ከሕ​ዝቡ ተለ​ይቶ ይጥፋ።”


እንደ እርሱ ያለ​ውን የሚ​ያ​ደ​ርግ ሰው፥ በሌ​ላም ሰው ላይ የሚ​ያ​ፈ​ስ​ሰው ከሕ​ዝቡ ተለ​ይቶ ይጥፋ።”


“ሰባት ቀን ቂጣ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያም ቀን እር​ሾ​ውን ከቤ​ታ​ችሁ ታወ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ቀን አን​ሥቶ እስከ ሰባ​ተ​ኛው ቀን እርሾ ያለ​በ​ትን እን​ጀራ የሚ​በላ ነፍስ ከእ​ስ​ራ​ኤል ተለ​ይቶ ይጥፋ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “ሚስ​ትህ ሦራ እን​ግ​ዲህ ሦራ ተብላ አት​ጠ​ራም፤ ስምዋ ‘ሣራ’ ይሆ​ናል እንጂ።


የዲና ወን​ድ​ሞች ስም​ዖ​ንና ሌዊም እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “እኅ​ታ​ች​ንን ላል​ተ​ገ​ረዘ ሰው ለመ​ስ​ጠት ይህን ነገር እና​ደ​ርግ ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ንም፤ ይህ ነውር ይሆ​ን​ብ​ና​ልና።


በዚ​ያ​ችም ቀን ራሱን የማ​ያ​ዋ​ርድ ሰው ሁሉ ከሕ​ዝቡ ተለ​ይቶ ይጥፋ።


ነገር ግን ንጹሕ የሆነ ሰው በመ​ን​ገ​ድም ላይ ያል​ሆነ ፋሲ​ካን ባያ​ደ​ርግ፥ ያ ሰው ከሕ​ዝቡ ዘንድ ተለ​ይቶ ይጠ​ፋል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቍር​ባን በጊ​ዜው አላ​ቀ​ረ​በ​ምና ያ ሰው ኀጢ​አ​ቱን ይሸ​ከ​ማል።


እን​ጀ​ራ​ዬን፥ ስብ​ንና ደምን በም​ታ​ቀ​ር​ቡ​በት ጊዜ በመ​ቅ​ደሴ ውስጥ ይሆኑ ዘንድ ቤቴ​ንም ያረ​ክሱ ዘንድ፥ በል​ባ​ቸ​ውና በሥ​ጋ​ቸው ያል​ተ​ገ​ረ​ዙ​ትን እን​ግ​ዶ​ችን ሰዎች አግ​ብ​ታ​ች​ኋ​ልና፥ በር​ኵ​ሰ​ታ​ች​ሁም ሁሉ ቃል ኪዳ​ኔን አፍ​ር​ሳ​ች​ኋ​ልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች