Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 17:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ሕፃ​ኑ​ንም በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ትገ​ር​ዙ​ታ​ላ​ችሁ፤ በቤት የተ​ወ​ለደ ወይም ከዘ​ራ​ችሁ ያይ​ደለ፥ በብ​ርም ከእ​ን​ግዳ ሰው የተ​ገዛ ወንድ ሁሉ በት​ው​ል​ዳ​ችሁ ይገ​ረዝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 የሚመጣውም ትውልድ ሁሉ፣ ማንኛውም ወንድ ልጅ፣ ስምንት ቀን ሲሞላው ይገረዝ፤ እንደዚሁም በቤትህ የተወለደውና ከውጭ በገንዘብ የተገዛ ባዕድ ሁሉ ይገረዝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 የስምንት ቀን ልጅ ይገረዝ፥ በቤት የተወለደ ወይም ከዘራችሁ ያልሆነ በብርም ከእንግዳ ሰው የተገዛ፥ ወንድ ሁሉ በትውልዳችሁ ይገረዝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በመጪው ዘመን የሚወለድ ወንድ ልጅ ሁሉ በተወለደ በስምንተኛው ቀን ይገረዝ፤ እንዲሁም በቤትህ የተወለዱና በቤትህ ሳይወለዱ ከውጪ በገንዘብ ተገዝተው የመጡ ባሪያዎች ሳይቀሩ በዚሁ ዐይነት ይገረዙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 የስምንት ቀን ልጅ ይገረዝ፤ በቤት የተወለደ ወይም ከዘራችሁ ያይደለ በብርም ከእንግዳ ሰው የተገዛ፥ ወንድ ሁሉ በትውልዳችሁ ይገርዝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 17:12
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንደ ግዳ​ጅዋ ወራት ትረ​ክ​ሳ​ለች። በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን ልጁ ከሥ​ጋው ሸለ​ፈት ይገ​ረዝ።


ስም​ንት ቀን በተ​ፈ​ጸመ ጊዜም ሕፃ​ኑን ሊገ​ዝ​ሩት ወሰ​ዱት፤ በማ​ኅ​ፀ​ንዋ ሳት​ፀ​ን​ሰው መል​አኩ እን​ዳ​ወ​ጣ​ለ​ትም ስሙን ኢየ​ሱስ አሉት።


በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን የተ​ገ​ዘ​ርሁ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ከብ​ን​ያም ነገድ ከዕ​ብ​ራ​ው​ያን ዕብ​ራዊ ነኝ፤ በኦ​ሪ​ትም ፈሪ​ሳዊ ነበ​ርሁ።


ከዚ​ህም በኋላ በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ሕፃ​ኑን ሊገ​ዝ​ሩት መጡ፤ በአ​ባ​ቱም ስም ዘካ​ር​ያስ ብለው ጠሩት።


በውኑ ለሰው ይም​ሰል አይ​ሁ​ዳዊ መሆን ይገ​ባ​ልን? ለሰው ፊትስ ተብሎ ይገ​ዘ​ሩ​አ​ልን?


የግ​ዝ​ረ​ት​ንም ኪዳን ሰጠው፤ ከዚ​ህም በኋላ ይስ​ሐ​ቅን ወለደ፤ በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀንም ገረ​ዘው፤ እን​ዲሁ ይስ​ሐ​ቅም ያዕ​ቆ​ብን፥ ያዕ​ቆ​ብም ዐሥራ ሁለ​ቱን የቀ​ደሙ አባ​ቶ​ችን ገረዙ።


አብ​ር​ሃ​ምም ልጁን ይስ​ሐ​ቅን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ገረ​ዘው።


አብ​ር​ሃ​ምም ልጁን ይስ​ማ​ኤ​ልን፥ በቤ​ቱም የተ​ወ​ለ​ዱ​ትን ሁሉ፥ በወ​ር​ቅም የገ​ዛ​ውን ወንድ ሁሉ፥ ከቤተ ሰቡም ወን​ዶ​ቹን ሁሉ ወሰደ። የሥ​ጋ​ቸ​ው​ንም ቍል​ፈት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ለው በዚ​ያው ቀን ገረዘ።


አገ​ል​ጋይ ወይም በብር የተ​ገዛ ቢኖር ከተ​ገ​ረዘ በኋላ ያን ጊዜ ከእ​ርሱ ይብላ።


እን​ዲ​ሁም በበ​ሬ​ዎ​ች​ህና በበ​ጎ​ችህ፥ በአ​ህ​ያ​ህም ታደ​ር​ገ​ዋ​ለህ፤ ሰባት ቀን ከእ​ናቱ ጋር ይቀ​መጥ፤ በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን ለእኔ ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች