Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 13:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 አብ​ራ​ምም በከ​ብት፥ በብ​ርና በወ​ርቅ እጅግ በለ​ጸገ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 አብራም በከብት፣ በብርና በወርቅ እጅግ በልጽጎ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 አብራምም በከብት በብርና በወርቅ እጅግ በለጠገ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 አብራም ብዙ እንስሶች፥ ብዙ ብርና ወርቅ ያለው ሀብታም ሰው ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 አብራምም በከብት በብርና በወርቅ እጅግ በለጠገ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 13:2
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለአ​ብ​ራ​ምም ስለ እር​ስዋ መል​ካም አደ​ረ​ጉ​ለት፤ ለእ​ርሱ በጎ​ችም፥ በሬ​ዎ​ችም፥ አህ​ዮ​ችም፥ በቅ​ሎ​ዎ​ችም፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ባሪ​ያ​ዎ​ችም፥ ግመ​ሎ​ችም ነበ​ሩት።


በአ​ን​ድ​ነ​ትም ይቀ​መጡ ዘንድ ምድር አል​በ​ቃ​ቸ​ውም፤ ንብ​ረ​ታ​ቸው ብዙ ነበ​ርና፤ ስለ​ዚ​ህም ባን​ድ​ነት ይቀ​መጡ ዘንድ ምድር አል​በ​ቃ​ቻ​ቸ​ውም።


አብ​ር​ሃ​ምም ሸመ​ገለ፤ ዘመ​ኑም አለፈ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን በሁሉ ባረ​ከው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጌታ​ዬን እጅግ ባረ​ከው፤ አገ​ነ​ነ​ውም፤ ላሞ​ች​ንና በጎ​ችን፥ ወር​ቅ​ንና ብርን፥ ወን​ዶች ባሪ​ያ​ዎ​ች​ንና ሴቶች ባሪ​ያ​ዎ​ችን፥ ግመ​ሎ​ች​ንና አህ​ዮ​ች​ንም ሰጠው።


ወን​ዶ​ችና ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ችን፥ ብዙ በጎ​ች​ንና ላሞ​ችን፥ የእ​ርሻ መሬ​ት​ንም ገዛ፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ሰዎ​ችም ቀኑ​በት።


ያዕ​ቆ​ብም እጅግ ባለ​ጠጋ ሆነ፤ ሴቶ​ችም ወን​ዶ​ችም አገ​ል​ጋ​ዮች፥ ብዙ ከብ​ትም፤ ላሞ​ችም፥ በጎ​ችም፥ ግመ​ሎ​ችና አህ​ዮ​ችም ሆኑ​ለት።


አንተ ቤቱን በው​ስ​ጥም በው​ጭም፥ በዙ​ሪ​ያው ያለ​ው​ንም ሁሉ አል​ሞ​ላ​ህ​ለ​ት​ምን? የእ​ጁ​ንም ሥራ ባር​ከ​ህ​ለ​ታል፥ ከብ​ቱ​ንም በም​ድር ላይ አብ​ዝ​ተ​ህ​ለ​ታል።


ከብ​ቶ​ቹም፦ ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመ​ሎች፥ አም​ስት መቶም ጥማድ በሬ፥ አም​ስት መቶም እን​ስት አህ​ዮች ነበሩ፤ እጅግ ብዙም አገ​ል​ጋ​ዮች ነበ​ሩት፤ ሥራ​ውም በም​ድር ላይ ታላቅ ነበረ፤ ያም ሰው በም​ሥ​ራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ገናና ነበረ።


የእግዚአብሔር በረከት በጻድቃን ራስ ላይ ሆና ባለጠጋ ታደርጋለች፥ ኀዘንንም ወደ ልብ አታመጣም።


ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።


ነገር ግን ዛሬ እንደ ሆነ ለአ​ባ​ቶ​ችህ የማ​ለ​ውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ እርሱ ኀይ​ልን ስለ​ሚ​ሰ​ጥህ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አስ​በው።


ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው፥ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድሀ ያደ​ር​ጋል፤ ባለ​ጠ​ጋም ያደ​ር​ጋል፤ ያዋ​ር​ዳል፤ ደግ​ሞም ከፍ ከፍ ያደ​ር​ጋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች