Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 13:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ተነሣ፤ በም​ድር በር​ዝ​መ​ቷም፥ በስ​ፋ​ቷም ዙር፤ እር​ስ​ዋን ለአ​ን​ተና ለዘ​ርህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እሰ​ጣ​ለ​ሁና።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እንግዲህ ምድሪቱን ስለምሰጥህ ተነሣ፤ በርዝመቷም፣ በስፋቷም ተመላለስባት።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ተነሣ፥ በምድር በርዝመትዋም በስፋትዋም ሂድ እርሷን ለአንተ እሰጣለሁና።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ተነሥተህ በምድሪቱ ስፋትና ርዝመት ሂድ፤ ሁሉንም ለአንተ እሰጥሃለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ተነሣ በምድር በርዝመትዋም በስፋትዋም ሂድ እርስዋን ለአንተ እሰጣለሁና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 13:17
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የም​ታ​ያ​ትን ምድር ሁሉ ለአ​ን​ተና ለዘ​ርህ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እሰ​ጣ​ለ​ሁና።


“ይህ​ችን ምድር ትወ​ር​ሳት ዘንድ እን​ድ​ሰ​ጥህ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር ያወ​ጣ​ሁህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ” አለው።


በው​ስ​ጥዋ የም​ት​ኖ​ር​ባ​ትን ይህ​ችን ምድር፥ የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር ሁሉ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይገ​ዙ​አት ዘንድ ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ለሁ፤ አም​ላ​ክም እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።”


እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላዩ ቆሞ​በት ነበር፥ እን​ዲ​ህም አለ፥ “የአ​ባ​ትህ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ የይ​ስ​ሐ​ቅም አም​ላክ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ አት​ፍራ፥ ይህ​ችን አንተ የተ​ኛ​ህ​ባ​ትን ምድር ለአ​ን​ተም ለዘ​ር​ህም እሰ​ጣ​ለሁ፤


ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን አላ​ቸው፥ “እኔ እሞ​ታ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መጐ​ብ​ኘ​ትን ይጐ​በ​ኛ​ች​ኋል፤ ከዚ​ህ​ችም ምድር ያወ​ጣ​ች​ኋል። ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም ወደ ማለ​ላ​ቸው ምድር ያገ​ባ​ች​ኋል።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ራራ​ላ​ቸው፤ ማራ​ቸ​ውም፤ ከአ​ብ​ር​ሃ​ምና ከይ​ስ​ሐቅ፥ ከያ​ዕ​ቆ​ብም ጋር ስላ​ደ​ረ​ገው ቃል ኪዳን እነ​ር​ሱን ተመ​ለ​ከተ፤ ሊያ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም አል​ወ​ደ​ደም፤ ፈጽ​ሞም ከፊቱ አል​ጣ​ላ​ቸ​ውም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ብ​ራም ተገ​ለ​ጠ​ለ​ትና፥ “ይህ​ችን ምድር ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ለሁ” አለው። አብ​ራ​ምም ለእ​ርሱ ለተ​ገ​ለ​ጠ​ለት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ መሠ​ው​ያን ሠራ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች