Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 13:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ሎጥ ከተ​ለ​የው በኋ​ላም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ​ራ​ምን አለው፥ “ዐይ​ን​ህን አን​ሣና አንተ ካለ​ህ​በት ስፍራ ወደ መስ​ዕና ወደ አዜብ፥ ወደ ምሥ​ራ​ቅና ወደ ምዕ​ራብ እይ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ሎጥ ከተለየው በኋላ እግዚአብሔር አብራምን እንዲህ አለው፤ “ካለህበት ስፍራ ቀና ብለህ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ፣ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ ተመልከት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ሎጥ ከተለየው በኋላም ጌታ አብራምን አለው፦ “ዓይንህን አንሣና አንተ ካለህበት ስፍራ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ እይ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ሎጥ ከሄደ በኋላ እግዚአብሔር አብራምን እንዲህ አለው፤ “ካለህበት ስፍራ ሆነህ ወደ ሰሜን፥ ወደ ደቡብ፥ ወደ ምሥራቅና ምዕራብ ተመልከት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ሎጥ ከተለየው በኍላም እግዚአብሔር አብራምን አለው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 13:14
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዐይ​ን​ሽን አን​ሥ​ተሽ በዙ​ሪ​ያሽ ተመ​ል​ከቺ፤ እነ​ዚህ ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው ወደ አንቺ ይመ​ጣሉ። እኔ ሕያው ነኝና እነ​ዚ​ህን ሁሉ እንደ ጌጥ ትለ​ብ​ሻ​ቸ​ዋ​ለሽ፤ እንደ ሙሽ​ራም ትጐ​ና​ጸ​ፊ​አ​ቸ​ዋ​ለሽ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን አት​ሻ​ገ​ር​ምና ወደ ተራ​ራው ራስ ውጣ፤ ዐይ​ን​ህ​ንም ወደ ባሕር ወደ መስ​ዕም፥ ወደ አዜ​ብም ወደ ምሥ​ራ​ቅም አን​ሥ​ተህ በዐ​ይ​ንህ ተመ​ል​ከት።


ዐይ​ኖ​ች​ሽን አን​ሥ​ተሽ በዙ​ሪ​ያሽ ተመ​ል​ከቺ፤ ልጆ​ች​ሽም እንደ ተሰ​በ​ሰቡ እነሆ፥ እዪ፤ ወን​ዶች ልጆ​ችሽ ከሩቅ ይመ​ጣሉ፤ ሴቶች ልጆ​ች​ሽ​ንም በጫ​ንቃ ላይ ይሸ​ከ​ሙ​አ​ቸ​ዋል።


ዘር​ህም እንደ ባሕር አሸዋ ይሆ​ናል፤ እስከ ባሕ​ርና እስከ አዜብ እስከ መስ​ዕና እስከ ምሥ​ራቅ ይበ​ዛል፤ ይሞ​ላ​ልም፤ የም​ድ​ርም ሕዝ​ቦች ሁሉ በአ​ንተ፥ በዘ​ር​ህም ይባ​ረ​ካሉ።


ሎጥም ዓይ​ኖ​ቹን አነሣ፤ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ዙሪያ ያለ​ው​ንም ሀገር ሁሉ ውኃ የሞ​ላ​በት መሆ​ኑን አየ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰዶ​ም​ንና ገሞ​ራን ከማ​ጥ​ፋቱ አስ​ቀ​ድሞ እስከ ሴጎር ድረስ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገነ​ትና እንደ ግብፅ ምድር እንደ ነበረ አየ።


ሙሴም ከሞ​ዓብ ሜዳ በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት ወዳ​ለው ወደ ናባው ተራራ ወደ ፈስጋ ራስ ወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እስከ ዳን ድረስ ያለ​ውን የገ​ለ​ዓ​ድን ምድር አሳ​የው፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች