Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 12:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ፈር​ዖ​ንም አብ​ራ​ምን ጠርቶ አለው፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ህ​ብኝ ምን​ድን ነው? እር​ስዋ ሚስ​ትህ እንደ ሆነች ለምን አል​ገ​ለ​ጥ​ህ​ል​ኝም?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ከዚያም ፈርዖን አብራምን አስጠርቶ እንዲህ አለው፤ “ይህ ያደረግህብን ነገር ምንድን ነው? ‘ሚስትህ እንደ ሆነች ለምን አልነገርኸኝም?’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ፈርዖንም አብራምን ጠርቶ አለው፦ ይህ ያደረግህብኝ ምንድነው? እርሷ ሚስትህ እንደ ሆነች ለምን አልገለጥህልኝም?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ከዚህ በኋላ ፈርዖን አብራምን አስጠርቶ እንዲህ ሲል ጠየቀው “ይህ ያደረግኽብኝ ነገር ምንድን ነው? ሣራይ ሚስትህ እንደ ሆነች ለምን አልነገርከኝም?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ፈርዖንም አብራምን ጠርቶ አለው፤ ይህ ያደረግህብኝ ምንድር ነው? እርስዋ ሚስትህ እንደ ሆነች ለምን አልገለጥህልኝም?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 12:18
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የንጉሥ ልብ እንደ ውኃ ፈሳሽ በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ ወደ ወደደውም ይመልሳታል፥ በዚያም ትቈያለች።


ሳኦ​ልም ዮና​ታ​ንን፥ “ያደ​ረ​ግ​ኸ​ውን ንገ​ረኝ” አለው፤ ዮና​ታ​ንም፥ “በእጄ ባለው በበ​ትሬ ጫፍ ጥቂት ማር በር​ግጥ ቀም​ሻ​ለሁ፤ እነ​ሆኝ፥ እሞ​ታ​ለሁ” ብሎ ነገ​ረው።


ኢያ​ሱም አካ​ንን፥ “ልጄ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ስጥ፤ ለእ​ር​ሱም ተና​ዘዝ፤ ያደ​ረ​ግ​ኸ​ው​ንም ንገ​ረኝ፤ አት​ሸ​ሽ​ገ​ኝም” አለው።


ሙሴም አሮ​ንን፥ “ይህን ታላቅ ኀጢ​አት ታመ​ጣ​በት ዘንድ ይህ ሕዝብ ምን አደ​ረ​ገህ?” አለው።


ዮሴ​ፍም፥ “ይህ ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ነገር ምን​ድን ነው? እንደ እኔ ያለ ሰው ምሥ​ጢ​ርን እን​ዲ​ያ​ውቅ አታ​ው​ቁ​ምን?” አላ​ቸው።


ላባም ያዕ​ቆ​ብን አለው፥ “ለምን እን​ዲህ አደ​ረ​ግህ? ከእኔ በስ​ውር የኰ​በ​ለ​ልህ? ልጆ​ች​ንስ ሰር​ቀህ በሰ​ይፍ እን​ደ​ማ​ረከ የወ​ሰ​ድ​ኻ​ቸው?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “ቃየል! ምን አደ​ረ​ግህ? የወ​ን​ድ​ምህ የአ​ቤል የደሙ ድምፅ ከም​ድር ወደ እኔ ይጮ​ሃል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ሴቲ​ቱን፥ “ይህን ለምን አደ​ረ​ግሽ?” አላት። ሴቲ​ቱም አለች፥ “እባብ አሳ​ተ​ኝና በላሁ።”


ለም​ንስ ‘እኅቴ ናት’ አልህ? ለእኔ ሚስት ትሆ​ነኝ ዘንድ ወስ​ጃት ነበር። አሁ​ንም እነ​ኋት፥ ሚስ​ትህ በፊ​ትህ ናት፤ ይዘ​ሃ​ትም ሂድ።”


በዚ​ያች ሌሊ​ትም አቤ​ሜ​ሌክ ተኝቶ ሳለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ልም ወደ እርሱ መጣ፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “እነሆ፥ አንተ ስለ ወሰ​ድ​ሃት ሴት ትሞ​ታ​ለህ፤ እር​ስዋ ባለ ባል ናትና።”


በነ​ጋም ጊዜ እነሆ ልያ ነበ​ረች፤ ያዕ​ቆ​ብም ላባን፥ “ምነው እን​ደ​ዚህ አደ​ረ​ግ​ህ​ብኝ? ያገ​ለ​ገ​ል​ሁህ ስለ ራሔል አል​ነ​በ​ረ​ምን? ለምን አታ​ለ​ል​ኸኝ?” አለው።


እና​ን​ተም በዚች ምድር ከሚ​ኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን አታ​ድ​ርጉ፤ ለአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አት​ስ​ገ​ዱ​ላ​ቸው፤ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ስበሩ፤ መሠ​ዊ​ያ​ቸ​ው​ንም አፍ​ርሱ አልሁ። እና​ንተ ግን ቃሌን አል​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ ይህ​ንስ ለምን አደ​ረ​ጋ​ችሁ?


ኢዮ​አ​ብም ወደ ንጉሥ ገብቶ፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ኸው ነገር ምን​ድን ነው? እነሆ፥ አበ​ኔር መጥ​ቶ​ልህ ነበር፤ በደ​ኅና እን​ዲ​ሄድ ስለ​ምን አሰ​ና​በ​ት​ኸው?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች